ሕይወትን_መጠበቅ (3) ‎ሰውን እግዚአብሔር ይፈውስሃል ከማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ባንተ ውስጥ አለ ማለት… — Sonship in Christ — TG.ME

‎#ሕይወትን_መጠበቅ (3)
‎ሰውን እግዚአብሔር ይፈውስሃል ከማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ባንተ ውስጥ አለ ማለት ይበልጥ ጉልበት ይሰጠዋል። ዔድን ከእግዚአብሔር ጋር ያልተገደበ ኅብረት የምናደርግበት መንፈሳዊ ስፍራችን ነው። ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ሕይወት ከእርሱ ጋር ባለን ኅብረት የሚቀጥል ነው። ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ባልተገደበ ኅብረት ውስጥ የሚያፈልገንን ሁሉ እናገኛለን። ሐዋርያ ጳውሎስ በ1ኛ ዮሐንስ መልዕክቱ ላይ “በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ በልቡ ምስክር አለው፤ ማንም እግዚአብሔርን የማያምን ሁሉ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ” (1ኛ ዮሐ 5: 10-13 አ.መ.ት) ብሎአል። #የዘላለም_ሕይወት_ማለት ለዘላለም መኖር ሳይኾን የእግዚአብሔርን ሕይወት መካፈል ነው። ከእግዚአብሔር ለመወለድ እሚያስፈልገው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ማመን ነው። መጽሐፍም
‎“ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፤ አባትንም የሚወድ ሁሉ ልጁንም እንደዚሁ ይወዳል” (1ኛ ዮሐ 5: 1 አ.መ.ት) ይላል።

‎ከእግዚአብሔር ተወልዶአል ማለት ከእግዚአብሔር ሕይወትን ተካፍሎአል ማለት ነው።
‎#ታዲያ_ለምንድነው ይኼ ሕይወት የምንፈልገውን ፍሬ ያላፈራው ?? ካልን ማልማት፥ መንከባከብ እና መጠበቅ የእኛ ድርሻ ስለኾነ ነው። መጽሐፍ ሲናገር “እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው” (ዘፍጥረት 2: 15 አ.መ.ት) ይላል።
‎የእኔና የእናንተ ገነታችን ከእግዚአብሔር የተካፈልነው ሕይወታችን ነው። ዓለም ውስጥ ገነት የለም ገነታችን የተካፈልነው ሕይወታችን ነው። የተሰጠንን ሕይወት እያለማን፥ እየተንከባከብን፥ እየጠበቅን እንደኾነ ሕይወታችን የምንፈልገውን ፍሬ ያፈራል፤ ይበዛልናል። ኢየሱስ ስለመምጣቱ ሲናገር “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐንስ 10፥10) ብሎአል።

‎ክርስቶስ የሰጠን ሕይወት የሚበዛ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ ነው። ነገር ግን የተሰጠንን ሕይወት ካላለማን፥ ካልተንከባከብን፥ ካልጠበቅን በጠላት ይወረሳል፥ ይያያዛል፤ ይበዘብዛል። ኢየሱስ የሰጠን ሙሉ (Full Package) እና Perfect ሕይወት ነው። ልክ አዳም ዔድን ሲገባ እንደነበረው ሁሉንም የያዘ ሕይወት ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጠን፤ ምንም እጥረት የለበትም። ነገር ግን ካልጠበቅን ለተሰጠን ዓላማ ልንጠቀም አንችልም።
‎ለምሳሌ፡- እግዚአብሔር የጠራን ለአገልግሎት ቢኾን ወይም ለኾነ ሥራ ቢኾን ያ ገነታችን ነው። አንድ ሰው የአገልግሎት ጥሪ እያለበት ባያገለግል በአገልግሎት ልያበዛ፥ ሊያተርፍ፥ ልያፈራ ያለውን ሕይወት ያቀጭጫል። ማንኛውም ከጌታ የተቀበልነው መልካም ነገር ገነታችን ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ስኬታማ እንዲንኾን ነው። እግዚአብሔር እጥረትን፥ ድህነትን ሳይኾን የሰጠን ሙላቱን (ሙሉነትን) ነው። መጽሐፍ “በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል”(2ኛ ጴጥ 1:3 አ.መ.ት) ይላል።

👉 በአዳም እና በእግዚአብሔር መካከል ጠቡ ለምን ከረረ ለምን በቀላሉ አልማረውም?? ብለን ብናስብ ፡-
‎#የመጀመሪያው ምክንያት በአዳምና በእግዚአብሔር መካከል ሰይጣን መግባቱ ነው። የሰይጣን ማንነትና አዳም ከሰይጣን ጋር አብሮ በእግዚአብሔር ላይ ማመጹ ነው።
‎መጽሐፍ ሲናገር “ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት” (1ኛ ጢሞ 2:14 አ.መ.ት) ይላል፤ አዳም በፈቃዱ ነው ሕይወቱን ለሰይጣን ያስገዛው። ሰይጣን ደግሞ የእግዚአብሔር የኾነውን ሁሉ ማጥፋትና ማበላሸት ነውና ዓላማው።

ይቀላቀላሉንhttps://t.me/TheimageofChrist1
ለሌሎች 👉👉shareማድረግን እና #Add👈👈 ማድረግን አትርሱ
❤1
August 15, 2025 318 2