#ሕይወትን_መጠበቅ (1)
የመጀመሪያው አዳም ከውድቀት በፊት በዔድን ሲኖር በመንፈሱ፥ በነፍሱም፥ በአካሉም ፍጹም ሕይወት ነበረው። እግዚአብሔር በዙሪያው የሚያስፈልገውን ሁሉ ከማዘጋጀት ባሻገር በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጅቶለት፤ አዳምን በዚያ በልዩነት አኑሮት ነበር (ዘፍ 2:8 አ.መ.ት)። እግዚአብሔር ለአዳም ምድራዊ ግዛትን ብቻ ሳይኾን ሕይወትን ነበር የሰጠው፤ ዔድን ሕይወት ነበረች። ዔድን የሕይወት Style ነው። ሰው ከውድቀቱ በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ያለማቋረጥ ኅብረት ማድረግ፥ ያለ ገደብ መስማትና መሰማት የሚችልበት ፍጹም ሰላማዊ የሕይወት Style ነበረው። እግዚአብሔር አዳምን በዔድን ሲያስቀምጥ እንዲያለማት፥ እንድንከባከባትና እንድጠብቃት ኀላፊነት ሰቶት ቢኾንም አዳም ኀላፊነቱን ባለመፈጸም በኀጢአት ከዔድን ወጣ። አዳም ዔድንን የማልማት፥ የመንከባከብና የመጠበቅ ኀላፊነቱን ባለመወጣት አትብላ የተባለውን በመብላት በአመጽ ምክንያት ወደቀ። ስለዚኽ መጽሐፍ ሲናገር ሰይጣን ወደ ዔድን መጣ ይለናል። መጽሐፍ ሰይጣን መጣ ስለን ወደ የኾነ ክልል ገባ እያለን ሳይኾን ከተቀበሉት ሕይወት ሊያጎላቸው መምጣቱን ይናገራል። ምክንያቱም ዔድን መኖሪያ ስፍራ ብቻ ሳይኾን በእግዚአብሔር የተቃኘ የሕይወት አይነት ነበር።
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለሰው እሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጠረ በኋላ ነው። ሰው ለምድር ሳይኾን የተፈጠረው ምድር ናት ለሰው የተፈጠረችው። አዳም ዔድንን እንድያለማት፥ እንድንከባከባትና እንድጠብቃት እግዚአብሔር ሲሰጠው የተሰጠውን ሕይወት የመጠበቅና የመንከባከብ ኅላፊነትም የእርሱ ነበር።
እግዚአብሔር አዳምን ጠብቀው ስል ይኼን ሕይወት ልቀማ ወይም ሊያበላሽ እሚፈልግ ጠላት፥ ሌባ አለ ማለቱ ነበር። ኢየሱስ ዲያብሎስ ሰራቂ ሌባ መኾኑን በአድስ ኪዳን ተናግሮአል። ሰይጣን ሊያሳጣን በዙሪያችን የሚያደባው ገንዘባችንን /ንብረታችንን ሳይኾን ያንን በእኛ ያለውን የእግዚአብሔርን ሕይወት (Zoe Life) ነው። ይኼንን ሕይወት አዳም መጠበቅ አቅቶት በኀጢአት ምክንያት ጣለው። መጽሐፍ የተታለለችው ሔዋን እንጂ አዳም እንዳልኾነ አዳም በፈቃዱ ሕይወቱን አሳልፎ እንደሰጠ ይናገራል (1ኛ ጢሞ 2፡ 14)። ለዚኽ ነው ያንን አዳም የጣለውን ሕይወት እግዚአብሔር ከሰይጣን በጉልበት ያልተቀበለው ምክንያቱም አዳም በፈቃዱ ነበር የሰጠው። ልክ ሰይጣን በእግዚአብሔርና በአዳም መካከል መግባት እንደማይችል ሁሉ በሰይጣንና በአዳም መካከል እግዚአብሔርም መግባት አልፈለገም ነበር። አዳም ሔዋን ፍሬውን አምጥታ ስትሰጠው ከየት አመጣሽ ? ማን ሰጠሽ ? ብሎ ጠይቋት እምቢም አላለም እንዲኹ በላው እንጂ። አዳም ፈቅዶ ፍሬውን እንደበላ ሰይጣን በሕጋዊ መንገድ ሕይወቱን አሳጣው (ከዔድን አስባረረው)። መጽሐፍ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ” (ሮሜ 5፥12) ይላል።
#ሁለተኛው_አዳም ግን ያመጣልን የእግዚአብሔርን አይነት ሕይወት ነው። ልክ የመጀመሪያው አዳም ከውድቀቱ በፊት የኖረውን ሕይወት ራሱን የጽድቅ ሕይወት ክርስቶስ ይዞልን መጣ።
#በጌታ ምጽአት ይኽ ስጋችን ስዋጅ (Redeemed ሲኾን) የሚሞተው ስጋ የማይሞተውን ሲለብስ ምንኖረው ሕይወት የመጀመሪያው አዳም ከውድቀት በፊት የኖረውን አይነት ሕይወት ነው። ከውድቀት በፊት አዳም በኖረው ሕይወት ሞት አልነበረም። ኢየሱስ ይዞልን የመጣው በትክክል አዳም በኀጢአት ያጣውን ሕይወት ነው። ስለዚኽ መጽሐፍ “ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” (1ኛ ቆሮ 15፥45)። “ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና” (1ኛ ቆሮ 15፡ 21-22) ይላል።
#በክርስቶስ_ያለን_ሕይወት_ነው። አዳም በመጀመሪያ የነበረውን ሕይወት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እንደገና ተቀብለናል፤ እኛ አሁን ሕይወት አለን፤ የእግዚአብሔር ሕይወት አለን። እኛ የተቀበልነው የማይጠፋ፥ የማይበላሽ የእግዚአብሔር ሕይወት ነው።
#አሁን ወደ ዔድን ተመልሰናል! #ዔድን አኗኗር እንጂ ስፍራ (Physical Location) አይደለም። ዔድን በአድስ ኪዳን የሕይወት አይነት ነው እንጂ ስፍራ አይደለም።
ይቀላቀላሉንhttps://t.me/TheimageofChrist1
ለሌሎች 👉👉shareማድረግን እና #Add👈👈 ማድረግን አትርሱ
August 14, 2025 319 1