ተማሪዎች https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ " ሙሉ ውጤታችን Disqualified ተደርጓል " ያሉ በርካታ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።
ተማሪዎቹ " ይፋ በተደረገው የፈተና ውጤት ላይ የገጠመን ከፍተኛ ችግር እንዲሰማልን እንፈልጋለን " ብለዋል።
ቅሬታቸውን ካቀረቡት መካከል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳንይንስ ተማሪዎች ውጤታቸው " ሙሉ በሙሉ Disqualified " የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ፥ በደብረ ብርሃን፣ ወሎ፣ አርባ ምንጭ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ሰመራ፣ ባህርዳር፣ ወልቂጤ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተለያዩ ተማሪዎች ውጤት ላይ ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው አመልክተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታቸውን ተመልክቶ ምክንያቱን በመለየትና በማሳወቅ እንዲሁም በመመርመር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና 53,620 ተፈታኞች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም
ለተማሪዎች በተማሪዎች




