Apple የመጀመሪያውን Foldable iPhone September ላይ ያስተዋውቃል
Apple ከ8 ዓመታት ገደማ ወሬ በኋላ የመጀመሪያውን foldable iPhone ለማስተዋወቅ ተቃርቧል
ስልኩ iPhone Fold ወይም iPhone Ultra ተብሎ ይጠራል ተብሎ ይጠበቃል
ይፋ የሚደረግበት ቀን September 9 ገደማ እንደሆነ ተነግሯል
ስልኩ ደግሞ ከ iPhone 18 Pro Pro Max እና Apple Watch Series 12 ጋር አብሮ ይጀምራል ተብሏል
ስልኩ ወደ ገበያ የሚወጣው September 18 ገደማ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል
ስልኩ book style foldable design ይኖረዋል
ይሄ ማለት ልክ እንደ Samsung Galaxy Z Fold አይነት ወደ ውስጥ የሚታጠፍ ንድፍ ይኖረዋል ማለት ነው
ተዘግቶ ሲታይ ካለፉት iPhones የበለጠ አራት ማዕዘን ቅርጽ ይኖረዋል ተብሏል
ውስጠኛው display ከ7,7 እስከ 7,8 ኢንች ገደማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል
ይሄ ልክ እንደ iPad mini screen 4ለ3 aspect ratio ይኖረዋል
ስልኩ A20 ወይም A20 Pro ቺፕ ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል
Dual 48MP ካሜራ ይኖረዋል ግን telephoto lens ላይኖረው ይችላል
Face ID ም ላይኖረው እንደሚችል ተነግሯል በምትኩ ሌላ authentication method ሊጠቀም ይችላል
ዋጋው ደግሞ በጣም ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል
ከ1,999 እስከ 2,399 ዶላር ገደማ ይደርሳል ተብሏል
ይሄ ከ Samsung Galaxy Z Fold8 (1,900 ዶላር) የበለጠ ውድ ያደርገዋል
Manufacturing ላይ ችግር ስለነበረ የመጀመሪያ አቅርቦት ውስን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል
ይሄ ማለት ስልኩ ሲወጣ በቀላሉ ማግኘት ላይሆን ይችላል ማለት ነው
ለምን ያገባናል
Apple ወደ foldable ገበያ በጣም ዘግይቶ እየገባ ነው
Samsung Huawei እና ሌሎች ኩባንያዎች ከዓመታት በፊት foldable ስልኮች አውጥተዋል
Apple ግን ሁልጊዜ technology ሙሉ በሙሉ እስኪበስል ድረስ ይጠብቃል ተብሎ ይታመናል
ይሄ ስልክ በኢትዮጵያ ገበያ ቢመጣ እንኳን ዋጋው በጣም ከፍተኛ ስለሚሆን ለጥቂት ሰዎች ብቻ ተደራሽ ይሆናል
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 27, 2026 321