OpenAI የራሱ Chip ሠራ Nvidia Blackwell ን በ Benchmark አለፈው
OpenAI Jalapeño የተባለውን የመጀመሪያ የራሱ AI chip ውጤት በ Hot Chips conference ላይ ይፋ አድርጓል
ውጤቱ Nvidia Blackwell ስርዓቶችን በልጦ ወጥቷል
Jalapeño ከ Broadcom ጋር በጋራ የተሠራ ሲሆን ለ inference ብቻ የተዘጋጀ ቺፕ ነው
Inference ማለት AI ሞዴል ራሱን ማሰልጠን ሳይሆን አስቀድሞ የተማረውን ተጠቅሞ መልስ የመስጠት ስራ ማለት ነው
ይሄ ስራ ChatGPT ጥያቄ በምትጠይቅበት ጊዜ ከበስተጀርባ የሚሠራው ሂደት ነው
SemiAnalysis የተባለ ገለልተኛ organization ውጤቱን አረጋግጧል
የ Jalapeño performance በ watt ከ1,5 እስከ 1,9 እጥፍ ገደማ ከ Nvidia Blackwell የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል
Latency ደግሞ ከ1,7 እስከ 3,6 እጥፍ ገደማ ያነሰ ተብሏል ይሄም መልስ በፍጥነት ይመጣል ማለት ነው
ሙከራው በ3 የተለያዩ AI ሞዴሎች ላይ ተደርጓል GPT OSS 120B DeepSeek R1 670B እና Kimi K2,5 1T
SemiAnalysis ውጤቱን Jalapeño smokes every other chip ብሎ ገልጾታል
OpenAI ግን ግልጽ ማድረግ የፈለገው ነገር አለ
ኩባንያው ከ Nvidia ጋር ያለውን ግንኙነት ማቆም እንዳልፈለገ ገልጿል
OpenAI አሁንም ከ Nvidia እና ከሌሎች partners chips መጠቀሙን እንደሚቀጥል አረጋግጧል
ይሄ ውጤት ግን ትልቅ ትርጉም አለው
OpenAI ራሱ ከ Nvidia ትልቅ ደንበኞች አንዱ ሆኖ ሳለ የራሱን ተወዳዳሪ ቺፕ ማምረት መቻሉ ትልቅ ነገር ነው
Analysts ይሄንን ለ Nvidia ትርፍ በተለይ በ inference ዘርፍ ስጋት ተብሎ ገልጸውታል
Jalapeño ገና በትንሽ መጠን በ2026 መጨረሻ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል
ትልቅ production ደግሞ በ2027 ይጀምራል ተብሏል
Nvidia's ቀጣይ ትውልድ Vera Rubin ደግሞ ገና አልተፈተነም
ለምን ያገባናል
ይሄ ውድድር ለ ተጠቃሚዎች ጥሩ ዜና ነው
AI ኩባንያዎች chip cost ሲቀንሱ AI tools ዋጋም ሊቀንስ ይችላል
ChatGPT ወይም ሌሎች OpenAI products የበለጠ ፈጣን እና ርካሽ ሊሆኑ ይችላሉ ማለት ነው
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 27, 2026 234 1