Xiaomi ራሱ የሠራው Xring O3 ቺፕ ከ Qualcomm የተሻለ ውጤት አሳየ
Xiaomi ራሱ የሠራውን አዲስ Xring O3 mobile chip ይፋ አድርጓል
ይሄ ቺፕ በ TSMC 3 nanometer manufacturing process የተሠራ ነው
Xring O3 በ AnTuTu benchmark ላይ 5,228,014 ነጥብ አስመዝግቧል
ይሄ ውጤት እስካሁን ከወጡ smartphone processors ሁሉ የላቀ ተብሎ ተመዝግቧል
ቺፕው ከ24 ቢሊዮን በላይ transistors ይዟል ይሄም ካለፈው Xring O1 ቺፕ 26 በመቶ ገደማ ጭማሪ ነው
ቺፕው LPDDR6 memory ን የሚደግፍ የመጀመሪያው mobile chip ነው
ይሄ አዲስ memory type እስከ 10,667 Mbps ፍጥነት ማድረስ ይችላል
ይሄ ካለፈው ትውልድ 48 በመቶ ገደማ የተሻለ bandwidth ነው
Xiaomi ተጨማሪ ሁለት ቺፖችንም አስተዋውቋል
Xring O100 የተባለው AI accelerator ለ Xiaomi ራሱ MiMo AI ሞዴል የተዘጋጀ ነው
Xring D100 ደግሞ ለ autonomous driving የተዘጋጀ ሲሆን ይሄ በ China የመጀመሪያው 3nm smart driving chip ነው
Xring O3 መጀመሪያ የሚገባው Xiaomi 18 Fold እና Pad 9 Pro Max ውስጥ ሲሆን በ September ይለቀቃል
የመጀመሪያው production ግን 200,000 እስከ 300,000 ስልኮች ብቻ ተብሎ ተገምቷል
Xiaomi ለዚህ ቺፕ ፕሮግራም ከ21 ቢሊዮን Yuan በላይ ኢንቨስት አድርጓል
ኩባንያው ወደ 3,000 ገደማ ኢንጂነሮች በዚህ ፕሮጀክት ላይ አሰማርቷል
ይሄ እርምጃ Xiaomi ን ከ Apple Samsung እና Huawei ጋር በራስ ቺፕ ልማት ተመሳሳይ ተወዳዳሪ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል
Xiaomi ቀድሞውኑ ከ Qualcomm እና MediaTek ቺፖች ላይ ጥገኝነትን ለመቀነስ እየሞከረ ነው
ለምን ያገባናል
ብዙ ኢትዮጵያውያን Xiaomi ስልኮችን ይጠቀማሉ
Xiaomi የራሱ ቺፕ ማልማት መቻሉ ወደፊት ስልኮች ላይ ዋጋ ተወዳዳሪነት እና performance ማሻሻል ሊያመጣ ይችላል
ምንም እንኳን Xring O3 መጀመሪያ ላይ premium ስልኮች ላይ ብቻ ቢውልም በጊዜ ሂደት ወደ mid-range ስልኮችም ሊስፋፋ ይችላል
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 26, 2026 154