Amazon Mechanical Turk ን ከ21 ዓመት በኋላ ዘጋው AI ራሱ የፈጠረውን ስራ በላው
Amazon Mechanical Turk የተባለውን አገልግሎቱን September 30 ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጋ አስታውቋል
ይሄ አገልግሎት ከ2005 ጀምሮ ለ21 ዓመታት ገደማ ሲሰራ ቆይቷል
Mechanical Turk ወይም MTurk ሰዎች ኮምፒውተር ማድረግ የማይችላቸውን ትንንሽ ስራዎች እንዲሠሩ ገንዘብ የሚከፍል platform ነው
ስራዎቹ ምስል መለየት survey መመለስ ወይም audio መጻፍ የመሳሰሉትን ያካትታሉ
Jeff Bezos ይሄንን አገልግሎት "artificial artificial intelligence" ብሎ ጠርቶት ነበር
ይሄ ውሳኔ ትልቅ አስቂኝ እውነታ ይዞ መጥቷል
Mechanical Turk የተሠራው ኮምፒውተሮች መስራት ስላልቻሉ ሰዎችን ለመጠቀም ነበር
አሁን ግን AI ራሱ እነዚያኑ ስራዎች በተሻለ ሁኔታ መስራት በመቻሉ platform ው ራሱ ጥቅም አልባ ሆኗል
ተጨማሪ አስገራሚ እውነታ ደግሞ አለ
በ2023 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው እስከ 46 በመቶ ገደማ የ MTurk ሠራተኞች ስራቸውን ለመስራት AI tools ሲጠቀሙ ነበር
ይሄ ማለት ሰዎች AI ን ለመተካት የተፈጠረውን platform እራሱ AI ን ተጠቅመው ሲያታልሉት ነበር ማለት ነው
MTurk ከ500,000 በላይ workers አገልግሏል
Amazon ባለፈው ወር አዳዲስ ደንበኞችን መቀበል አቁሞ ነበር ይሄም መዘጋቱን አመልካች ነበር
የ MTurk መዘጋት ቦታ ደግሞ Scale AI Mercor እና Prolific የተባሉ አዳዲስ AI-native data labeling ኩባንያዎች እየተኩ ነው
እነዚህ ኩባንያዎች ለ AI ሞዴል training የተሻለ human feedback ለማቅረብ ተወዳድረው እየሠሩ ነው
ለምን ያገባናል
ይሄ ታሪክ AI ኢንዱስትሪው ምን ያህል በፍጥነት እየተቀየረ እንዳለ ያሳያል
ከ20 ዓመት በፊት ሰው ለ AI ማሰልጠኛ ስራ ያስፈልግ ነበር
አሁን ግን AI ራሱ ያንን ስራ የተሻለ ስለሚሠራ ያ ስራ እየጠፋ ነው
ይሄ ለ ማንኛውም remote/online ስራ ላይ ለተመረኮዘ ሰው ጠቃሚ ማስጠንቀቂያ ነው AI ችሎታ በፍጥነት እያደገ ስለሆነ
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
1August 26, 2026 184