Amazon Echo Kindle እና Fire TV ዋጋ እስከ 60 በመቶ ጨመረ RAMageddon ተባለ
Amazon ያለ ምንም ማስታወቂያ Echo Kindle Fire TV እና eero devices ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል
ይሄ ውሳኔ ቀደም ብለን በተደጋጋሚ ካየነው የ memory chip እጥረት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው
Echo Dot ዋጋ ከ49,99 ዶላር ወደ 79,99 ዶላር ጨምሯል ይሄም 60 በመቶ ገደማ ጭማሪ ነው
Kindle 16GB ደግሞ ከ109,99 ዶላር ወደ 149,99 ዶላር ጨምሯል
Kindle Paperwhite ከ159,99 ዶላር ወደ 199,99 ዶላር ደርሷል
Fire TV Stick 4K Max ደግሞ ከ59,99 ዶላር ወደ 84,99 ዶላር ገደማ 42 በመቶ ገደማ ጨምሯል
Amazon ምክንያቱን ሲያስረዳ የ memory እና storage component ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ ለረጅም ጊዜ ተሸክመን ቆይተን ነበር ብሏል
ኩባንያው አሁን ግን ይሄንን ጭማሪ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ግድ ሆኖበታል
አስገራሚው ነገር ደግሞ Amazon ራሱ የዚህ ችግር አንድ ምክንያት ተባባሪ መሆኑ ነው
ኩባንያው በ2026 ውስጥ 220 ቢሊዮን ዶላር ለ AI data centers ኢንቨስት እያደረገ ነው ይሄም memory chip ፍላጎትን ከፍ የሚያደርግ ነው
Amazon ብቻ አይደለም ይሄንን እያደረገ ያለው
Apple በ ሰኔ ወር iPad እና MacBook ዋጋ ጨምሯል
Microsoft ደግሞ Xbox ዋጋ በ100 እስከ 150 ዶላር ጨምሯል 2 terabyte storage ስሪትን ደግሞ ሙሉ በሙሉ አቁሟል
Dell HP Lenovo እና Asus ተመሳሳይ ውሳኔ አድርገዋል
Analysts ይሄንን ቀውስ RAMageddon ብለው እየጠሩት ነው
ይሄ ቀውስ እስከ 2028 ወይም ከዚያ በላይ ሊቀጥል እንደሚችል ይገመታል
Microsoft እንደው ደግሞ ዋጋ በ2027 መጨረሻ ላይ ሊደገፍ ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል
ለምን ያገባናል
ይሄ ዋጋ ጭማሪ ቀደም ብለን የጻፍንባቸውን articles እውነታ ያረጋግጣል
የ smartphone laptop እና electronics ዋጋ በኢትዮጵያ ገበያም ተመሳሳይ ጭማሪ ሊያሳይ ይችላል
Electronics ለመግዛት ካቀድክ ገበያው ከፍ ከማለቱ በፊት ውሳኔ ብታደርግ የተሻለ ሊሆን ይችላል
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 25, 2026 222