TECH HABESHA: post #225 — TG.ME

Claude ዛሬ Down ሆኗል AI ገበያ ደግሞ ትልቅ ለውጥ እያሳየ ነው
Anthropic ኩባንያ ዛሬ August 24 ላይ Claude AI ላይ ችግር እንዳለ አረጋግጧል
ችግሩ Mythos 5 Fable 5 እና Opus 5 ሞዴሎችን የነካ ሲሆን ኩባንያው elevated error rates እያጋጠመው መሆኑን ገልጿል
ችግሩ የተጀመረው ጠዋት 5 ሰዓት UTC ገደማ ነው
Claude,ai API Claude Code እና Cowork በዋናነት ተጎድተዋል
Console እና Claude for Government ግን ያለ ችግር እየሰሩ ናቸው
Anthropic ትክክለኛውን ምክንያት ወይም መቼ እንደሚስተካከል እስካሁን በይፋ አላሳወቀም
ተጠቃሚዎች ችግሩ እስኪስተካከል ድረስ ChatGPT ወይም Gemini መጠቀም ጊዜያዊ አማራጭ ሊሆን ይችላል ተብሏል
ይሄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለ Claude ተደጋጋሚ ችግር እየሆነ መጥቷል
በሌላ በኩል ደግሞ የ AI ገበያ ድርሻ አሃዞች ትልቅ ለውጥ እያሳዩ ነው
በ2026 ግንቦት ወር መረጃ መሠረት ChatGPT 53,9 በመቶ የዓለም ገበያ ድርሻ ይዞ አሁንም ቀዳሚ ነው
ነገር ግን ይሄ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 79 በመቶ ገደማ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል
Gemini 27,9 በመቶ ገደማ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ450 በመቶ ገደማ አድጓል
Claude ደግሞ 9,2 በመቶ ገደማ የዓለም ገበያ ድርሻ ይዞ ሦስተኛ ቢሆንም እድገቱ ከሁሉም የበለጠ ፈጣን ነው
Claude ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ855 በመቶ ገደማ አድጓል
በተጨማሪ Claude በ enterprise ወይም የቢዝነስ ደንበኞች ዘንድ 70 በመቶ ገደማ ድርሻ ይዞ ቀዳሚ እንደሆነ ተነግሯል
ለምን ያገባናል
ይሄ ውድድር ለ ተጠቃሚዎች ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ኩባንያዎች እርስ በርስ ለመወዳደር ዋጋ እየቀነሱ እና feature እየጨመሩ ነው
ግን ዛሬ እንደታየው outages እንደዚህ አይነት ችግሮች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ለ አስፈላጊ ስራ ብቻ በአንድ AI tool ላይ ብቻ መደገፍ አደገኛ ሊሆን ይችላል
ብዙ ገንቢዎች እና ተጠቃሚዎች ከአንድ በላይ AI tools ተጠቅመው alternative እንዲኖራቸው ይመከራል

ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም

TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 24, 2026 187