TECH HABESHA: post #224 — TG.ME

Chinese Humanoid Robot የ Usain Bolt ን 100 ሜትር ክብረወሰን ሰበረ
በ Beijing በተካሄደው World Humanoid Robot Games ላይ አስደናቂ ክስተት ተፈጥሯል
Tiangong Ultra የተባለ Chinese humanoid robot 100 ሜትር በ9,39 ሰከንድ ውስጥ ሮጧል
ይሄ ውጤት በ2009 Usain Bolt ያስመዘገበውን የ9,58 ሰከንድ የዓለም ክብረወሰን በልጦታል
ከ Tiangong ሌላ Honor የተባለ የ smartphone ኩባንያ ያመረተው Lightning የተባለ ሌላ robot ደግሞ 9,47 ሰከንድ አስመዝግቧል
ይሄም እንዲሁ Bolt ን በልጦታል
Lightning ቀደም ብሎ በ test run ላይ ደግሞ 9,32 ሰከንድ አስመዝግቦ ነበር በሰዓት 52 ኪሎ ሜትር ገደማ ፍጥነት ደርሶ
ጨዋታው ግን ያለ ችግር አልነበረም
Robots ውድድሩን ከጨረሱ በኋላ ራሳቸውን ማቆም ስላልቻሉ ወደ ግድግዳ ተጋጭተው ወድቀዋል
ከዚያ በኋላ በstretcher ተወስደዋል ልክ እንደ ተጎዱ ስፖርተኞች
በተጨማሪ standing high jump ውድድር ላይ ሌላ robot 2,88 ሜትር በመዝለል ያለውን የ2,45 ሜትር human record በልጦታል
ውድድሩ በአጠቃላይ ከ2,000 በላይ humanoid robots ከ16 ሀገራት ተካፍለውበታል
Beijing ይሄንን ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ መሻሻል ታይቷል
ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ውድድር ላይ አሸናፊው robot 100 ሜትር የጨረሰው በ21,50 ሰከንድ ነበር
ይሄ ውጤት China በ humanoid robotics ዘርፍ እያደረገች ያለውን ፈጣን እድገት ያሳያል
US Government ግን ከዚህ ቀደም በ national security ስጋት ምክንያት የ Chinese humanoid robots import እንዳይገባ አግዷል
ለምን ያገባናል
ይሄ ክስተት AI እና robotics ቴክኖሎጂ ምን ያህል በፍጥነት እየገሰገሰ እንዳለ ያሳያል
ምንም እንኳን Ethiopia ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ባይኖረውም ወደፊት humanoid robots በ manufacturing logistics እና በሌሎች industries ውስጥ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ፍንጭ ይሰጣል

ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም

TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 24, 2026 170