Stripe OpenRouter ን በ7,5 ቢሊዮን ዶላር ገዛ AI ገንዘብ ፍሰት ገበያ ውስጥ ገባ
Stripe የተባለው ግዙፍ payment ኩባንያ OpenRouter ን ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል
ዋጋው ከ7,5 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ተዘግቧል
OpenRouter ገንቢዎች ከ400 በላይ AI ሞዴሎችን በአንድ API ብቻ እንዲደርሱ የሚያስችል platform ነው
ገንቢዎች በዋጋ ፍጥነት ወይም ጥራት መሠረት ወደ ተለያዩ ሞዴሎች እንዲቀያየሩ ያግዛል
ኩባንያው በቀን ከ10 ትሪሊዮን በላይ tokens ያስተናግዳል ከ10 ሚሊዮን በላይ ገንቢዎችም ይጠቀሙበታል
ይሄ ዋጋ ትልቅ ጭማሪ ያሳያል
OpenRouter ልክ ሦስት ወራት በፊት ብቻ በ1,3 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ 113 ሚሊዮን ዶላር funding አግኝቶ ነበር
አሁን ያለው ዋጋ ከዚያ 5 እጥፍ ገደማ ከፍ ያለ ነው
Stripe CEO Patrick Collison Tokens ለ AI ኩባንያዎች ማዕከላዊ ገንዘብ አይነት ናቸው ብሏል
Stripe ይሄንን ግዢ በማድረግ ኩባንያዎች የ AI ወጪያቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተዳድሩ ለማገዝ አቅዷል
ይሄ ግዢ ግን ጥያቄዎችንም አስነስቷል
OpenRouter ቀደም ሲል ገለልተኛ (neutral) routing ይሰጣል ተብሎ ይታመን ነበር
አሁን ግን Stripe ራሱ ከ OpenAI እና Anthropic ጋር የ ንግድ ግንኙነት ስላለው ገለልተኝነቱ ላይ ጥያቄ እየተነሳ ነው
በተጨማሪ ከ OpenRouter traffic ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ወደ Chinese AI ሞዴሎች እንደ DeepSeek የሚሄድ በመሆኑ ይሄ ጉዳይ ውስብስብ አድርጎታል
ለምን ያገባናል
ይሄ ግዢ AI infrastructure ኢንዱስትሪው ምን ያህል በፍጥነት እያደገ እንዳለ ያሳያል
ለ ኢትዮጵያ ገንቢዎች OpenRouter የመሰሉ tools ብዙ AI ሞዴሎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት ጠቃሚ ናቸው
Stripe ባለቤት ከሆነ በኋላ አገልግሎቱ እንዴት ሊቀየር እንደሚችል መከታተል ተገቢ ነው
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 24, 2026 69