የ Smartphone ሽያጭ በ2026 በ14 በመቶ ይቀንሳል Chip ዋጋ መጨመር ትልቁ ምክንያት
ዓለም አቀፍ የ smartphone ገበያ በ2026 ትልቅ መቀነስ እንደሚያሳይ አዲስ ጥናት አመልክቷል
Shipment ቁጥር ከ2025 ጋር ሲነጻጸር ከ14 በመቶ በላይ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል
አጠቃላይ ቁጥር ወደ 1,07 ቢሊዮን ስልኮች ገደማ ይደርሳል
ይሄ ካለፉት አስር ዓመታት ዝቅተኛው ቁጥር ነው
ዋናው ምክንያት ቀደም ብለን ባየነው የ memory chip እጥረት ተያይዞ የመጣ ነው
DRAM እና NAND ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ ኩባንያዎች የ production ወጪያቸው ጨምሯል
ተጨማሪ በ Iran ጦርነት ምክንያት የተፈጠረ logistics መስተጓጎልም ተጽዕኖ አድርጓል
Samsung ደግሞ ትልቅ ለውጥ ሊያሳይ ይችላል
ኩባንያው በ2026 ከ Apple ቀድሞ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ተገምቷል
ይሄም በ22,6 በመቶ market share Apple ን በ0,1 በመቶ ብቻ በልጦ ነው
ትልልቅ ኩባንያዎች እንደ Apple Google Samsung እና የ China brands ቀድሞውኑ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል
ተጨማሪ የዋጋ ጭማሪዎችም በቀጣይ product cycles ውስጥ ይጠበቃሉ
ባለሙያዎች እንደሚሉት ይሄ የ chip ዋጋ ችግር በ2026 ስልኮች specs ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል
አንዳንድ ኩባንያዎች RAM መጠን ወደ ኋላ የመመለስ አዝማሚያ ሊያሳዩ ይችላሉ ይሄም ከ2020 ወዲህ ያልታየ ክስተት ነው
ለምን ያገባናል
ይሄ መረጃ ቀደም ብለን የተነጋገርንበትን ርዕስ ያጠናክራል
በኢትዮጵያ ገበያ ስልክ ዋጋ ወደፊት ተጨማሪ ሊጨምር እንደሚችል ይሄ ጥናት ያረጋግጣል
Global shipment በመቀነሱ ምክንያት ደግሞ አንዳንድ models ማግኘት ራሱ ከባድ ሊሆን ይችላል
አዲስ ስልክ ለመግዛት ካቀድክ ውሳኔህን ቶሎ ማድረግ የተሻለ ሊሆን ይችላል
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 23, 2026 79