GitHub ለ8 ሰዓት ያክል ወድቆ ነበር ምክንያቱን አብራራ
GitHub August 17 ቀን ለ8 ሰዓት ገደማ ከባድ outage አጋጥሞት ነበር
ኩባንያው አሁን ምክንያቱን በዝርዝር አብራርቷል
Outage ው GitHub,com ን ብቻ ሳይሆን API Issues Pull Requests Actions authentication እና Copilot ን ጭምር ነካ
GitHub እንደገለጸው ችግሩ በአዲስ code deployment ወይም configuration change ምክንያት አልነበረም
ይልቁንም peak traffic የኩባንያውን Central US data center infrastructure በላይ ሆኖበት ነው
አንድ ወሳኝ component በበቂ ፍጥነት scale ማድረግ ባለመቻሉ ችግሩ ተፈጠረ
በችግሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ web እና API error rates ወደ 20 በመቶ ገደማ ደርሰው ነበር
Archive እና raw content downloads ደግሞ እስከ 50 በመቶ ገደማ error ደርሶባቸው ነበር
ችግሩን ይበልጥ ያወሳሰበው retry behavior ነው
ተጠቃሚዎች እና systems ደጋግመው ሲሞክሩ ተጨማሪ traffic ፈጠረ በተለይ ደግሞ ከCopilot ጋር በተያያዘ
ይሄ outage GitHub ለ ገንቢዎች cloud platforms CI/CD systems እና AI coding agents ምን ያህል ወሳኝ infrastructure እንደሆነ በግልጽ አሳይቷል
GitHub ሲወድቅ ችግሩ ከራሱ አልፎ ወደ ብዙ ሌሎች systems ሊዛመት እንደሚችል ይሄ ክስተት አሳይቷል
ለምን ያገባናል
ብዙ ኢትዮጵያውያን ገንቢዎች ለ daily work GitHub ን ይጠቀማሉ
ኮድ ለማስቀመጥ ለ team collaboration እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለ AI coding tools እንደ Copilot መሠረት ሆኖ ያገለግላል
እንደዚህ አይነት outage ሲያጋጥም ስራ ሙሉ በሙሉ ሊስተጓጎል ስለሚችል ገንቢዎች backup plan ወይም local git setup ቢኖራቸው ይመከራል
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም
TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 22, 2026 70