TECH HABESHA: post #219 — TG.ME

Meta Glimmer የተባለ አዲስ Open Weight AI ሞዴል ለቀቀ
Meta በዚህ ሳምንት Glimmer የተባለ አዲስ AI ሞዴል ይፋ አድርጓል
ይሄ ሞዴል ማንኛውም ሰው አውርዶ በራሱ hardware ላይ ማስኬድ የሚችል open weight ሞዴል ነው
Glimmer ከ Meta ጠንካራ ሞዴል Muse Spark የተለየ ነው
Muse Spark ኃይለኛ ቢሆንም Meta's API ውስጥ ብቻ ተቆልፎ የሚቀር ነው
Glimmer ግን ክፍት ሆኖ ማንም ገንቢ ሊጠቀምበት ይችላል
Meta CEO Mark Zuckerberg ከ ይፋ ማድረጉ ጋር በጻፈው ደብዳቤ AI ለሁሉም ሰው ክፍት መሆን አለበት የሚል ሀሳብ አንጸባርቋል
AI የወደፊት አቅጣጫ በጥቂት ላቦራቶሪዎች ብቻ መወሰን የለበትም ብሏል
ይሄ ውሳኔ ቀደም ብለን ካየነው Alibaba Qwen ስኬት ጋር ተመሳሳይ አዝማሚያ ያሳያል
ትልልቅ ኩባንያዎች ኃይለኛ ትንሽ ሞዴሎችን ክፍት እያደረጉ ትንንሽ ገንቢዎች እና ኩባንያዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ ነው
ይሄ ማለት ግን ምንም ገደብ የለውም ማለት አይደለም
Meta Glimmer ን ክፍት ቢያደርግም በጣም ኃይለኛውን Muse Spark ሞዴል ግን አሁንም በራሱ API ብቻ ይዞ ቆይቷል
ይሄ ለ ነጻ AI ያለውን ራዕይ የተወሰነ ገደብ እንዳለው ያሳያል
ለምን ያገባናል
ለ ኢትዮጵያ ገንቢዎች እና ለ small businesses ይሄ ጥሩ ዜና ነው
Glimmer ን ውድ cloud subscription ሳያስፈልግ በራስ ኮምፒውተር ወይም server ላይ ማስኬድ ይቻላል
ይሄ chatbot ወይም AI-powered app መስራት ለሚፈልጉ ሰዎች ወጪ ቆጣቢ አማራጭ ይሰጣል

ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም

TECH HABESHA
Techhabesha.com.et
@techhabeshas
August 21, 2026 69