TECH HABESHA: post #216 — TG.ME

የ RAM Chip ዋጋ ችግር መሻሻል ሊጀምር እንደሚችል ተስፋ ተሰጠ
ቀደም ብለን የ memory chip እጥረት የስልክ እና ላፕቶፕ ዋጋ እያናረ መሆኑን ተመልክተን ነበር
አሁን ግን ትንሽ ተስፋ ሰጪ ዜና ወጥቷል
TrendForce የተባለ የ market research ኩባንያ አዲስ ሪፖርት አውጥቷል
ሪፖርቱ እንደሚያሳየው DDR5 16GB memory module ዋጋ በ2026 መጨረሻ ገደማ ወደ መደበኛው ደረጃ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ አለ
ይሄ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ትንበያ አይደለም
Analysts ግን የ supply chain ውጥረት ቀስ በቀስ እየተለሳለሰ እንደሆነ እያመለከቱ ነው
ምንም እንኳን ይሄ ተስፋ ሰጪ ዜና ቢሆንም አሁንም ማስጠንቀቂያ አለ
Memory stocks እንደ Micron Technology SK Hynix እና Sandisk በቅርቡ በ premarket trading ውስጥ ዋጋቸው ወርዷል
ይሄ ማለት ገበያው ራሱ ስለ future stability እርግጠኛ አይደለም ማለት ነው
የ AI data centers የሚያስፈልጋቸው memory chip ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ ነው
ስለዚህ ዋጋ ወደ ቀድሞው ደረጃ ሙሉ በሙሉ የሚመለስበት ጊዜ እርግጠኛ አይደለም
ለምን ያገባናል
በኢትዮጵያ ገበያ አዲስ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ለመግዛት ካቀድክ ይሄ ዜና ትንሽ ተስፋ ይሰጣል
ነገር ግን ገበያው አሁንም ያልተረጋጋ ስለሆነ ወዲያውኑ ዋጋ ይቀንሳል ብሎ መጠበቅ ትክክል አይደለም
ካስፈለገህ ስልክ ወይም ላፕቶፕ አሁኑኑ ብትገዛ የተሻለ ሊሆን ይችላል በተለይ ካልቻልክ እስከ 2027 ድረስ መጠበቅ
ይሄንን ርዕስ ተከታትለን ተጨማሪ መረጃ ሲወጣ እናሳውቃለን
ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ ሁሌም

TECH HABESHA

Techhabesha.com.et
August 20, 2026 118