Zoom ን አሁኑኑ Update አድርግ Zoomsday የተባለ አደገኛ ደህንነት ችግር ተገኝቷል Zoom ኩባንያ አራት የደህንነት ችግሮችን የሚያርም update ለቋል ከነዚህ ውስጥ አንዱ Zoomsday ተብሎ
የተሰየመው በጣም አደገኛ እንደሆነ ተነግሯል
ይሄ ችግር በZoom annotation feature ውስጥ ይገኛል
Annotation ማለት በስክሪን sharing ወቅት ተጫዋቾች መሳል highlight ማድረግ ወይም ጽሁፍ መጨመር የሚያስችል tool ነው
ችግሩ አደገኛ የሚያደርገው ተጠቃሚው ምንም click ወይም download ማድረግ ሳይፈልግ ጥቃት ሊደርስበት መቻሉ ነው
Meeting ውስጥ ያለ ማንኛውም ተጫዋች annotation feature ን በመጠቀም ወደ ሌላ ተጠቃሚ ኮምፒውተር ላይ code መስራት ይችላል
ምንም visible warning ወይም ማስጠንቀቂያ ለተጠቃሚው አይታይም
ይሄ ችግር Zoom Workplace app ላይ በWindows Mac iOS Android እና Linux ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ አለው
ስለዚህ ማንኛውም device የሚጠቀም ሰው ተጠቂ ሊሆን ይችላል
Zoom እስካሁን ማንም ይሄንን ችግር ተጠቅሞ ጥቃት እንዳደረሰ የሚያሳይ ማስረጃ አላገኘም
ነገር ግን ችግሩ ምንም interaction ስለማይፈልግ security experts ወዲያውኑ update ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል
ተጨማሪ አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ ችግሩን ያገኙት researchers AI tools ተጠቅመው በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ ሙሉ exploit መስራት መቻላቸው ነው
ይሄ AI cybersecurity research ን ምን ያህል በፍጥነት እየቀየረ እንዳለ ያሳያል
Download Tech Habesha App: https://www.techhabesha.com.et/ https://techhabesha.com.et/
Tech Habesha
Tech Habesha - Technology news and articles

August 15, 2026 82