Google Pixel 11 ተመረቀ Tensor G6 እና Gemini AI ይዞ መጣ Google በኒው ዮርክ ትናንት ነሐሴ 12 ባደረገው Made by Google 2026 ኩነት ላይ Pixel 11 series ን ይፋ አድርጓል
ኩነቱን Trevor Noah የመራው ሲሆን Stephen Curry Alex Cooper እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል
Google Pixel 11 Pixel 11 Pro Pixel 11 Pro XL እና Pixel 11 Pro Fold የተባሉ አራት ስልኮችን አስተዋውቋል
ከስልኮቹ ጋር Pixel Watch 5 እና Pixel Tag የተባለ አዲስ tracker device አብረው ቀርበዋል
ትልቁ ለውጥ አዲሱ Tensor G6 ቺፕ ነው
ይሄ ቺፕ በ2 nanometer technology የተሰራ ሲሆን ይሄ ለ Pixel series ትልቁ chip upgrade ተብሎ ተገልጿል
ይሄ ማለት ስልኩ በተሻለ ፍጥነት እና ባነሰ battery ፍጆታ መስራት ይችላል ማለት ነው
Google በተጨማሪ Titan M3 የተባለ አዲስ security chip አስተዋውቋል
ይሄ chip ለ post quantum encryption የተዘጋጀ ሲሆን ስልኩ የወደፊት የ security ስጋቶችን መቋቋም እንዲችል ያግዘዋል
Gemini AI ደግሞ በስልኮቹ ውስጥ ጠልቆ ገብቷል
Sign to text የተባለ አዲስ feature በGboard እና Live Translate ውስጥ ታክሏል
ይሄ feature የASL sign language ን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ሲሆን ወደፊት ለሌሎች ሀገራት sign languages ም እንደሚስፋፋ ተገልጿል
Google እንደ Apple Tap to Share አይነት feature ን ኮፒ አድርጎ ወደ Quick Share ጨምሯል
Download Tech Habesha App: https://www.techhabesha.com.et/ https://techhabesha.com.et/
Tech Habesha
Tech Habesha - Technology news and articles

August 13, 2026 79