ለሌክ ሳይድ አካዳሚ ተማሪ ወላጆች
ጉዳዩ፦የተርም (በየ3ወር) እንዲከፈል የተወሰነዉን ዉሳኔ በድጋሚ ማጤን ይሆናል።
በመግቢያዉ ላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ቀደም ሲል በቀን 13-12-2018 በተፃፈዉ ማስታወቂያ መሰረት የ2019 ዓ/ም የት/ቤት ክፍያ በየ3 ወሩ ወይም በተርም እንዲከፈል መወሰኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የተለያዩ የት/ቤታችን ወላጆች በሰጡት አስተያየት አብዛኛው ወላጅ በወር ደመወዝ የሚተዳደርና በመካከለኛ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ክፍያዉን ለመፈፀም የሚቸገር መሆኑን በመግለፃቸዉ ት/ቤቱ ጉዳዩን እንደገና በማጤንና ችግሩን ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት የክፍያ ስርዓቱ ቀደም ሲል እንደነበረዉ እንዲቀጥል እና መክፈል የሚችል ወላጅ ግን በተርም፣በሴሚስተር ወይም የአመቱን አንድ ጊዜ መክፈል የሚችል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ት/ቤቱ
#.ሌክ ሳይድ አካዳሚ
#.ሐዋሳ ኢትዮጵያ





