የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የ2019 ዓ.ም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባ አጀማመር ግምገማ አደረገ።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የመጀመሪያ ቀን የምዝገባ አጀማመር እና ምዝገባውን በበይነ መረብ ከማከናወን አንጻር የሚያጋጥመውን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችን ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በውይይቱ መድረክ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ደሳለኝ የተገኙ ሲሆን ኃላፊውም በመልዕክታቸው የተማሪ ምዝገባ በወቅቱ አለማጠናቀቅ ለትምህርት ብክነት የሚዳርግ በመሆኑ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ምዝገባውን በተያዘው ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የመማር ማስተማር ስራ በካላንደሩ መሰረት ለመጀመር መዘጋጀት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

























