ለነብዩ ሙሀመድ ጠላቶች እነሆ መርዶ! አውሮፓ በሙሀመድ እየተጥለቀለቀች ነው።በአውሮፓ በከፍተኛ ፍጥነት… — Seid Social — TG.ME

ለነብዩ ሙሀመድ ጠላቶች እነሆ መርዶ!

አውሮፓ በሙሀመድ እየተጥለቀለቀች ነው።በአውሮፓ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኘው እስልምናና ተወዳጅነታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ያለው ነብዩ ሙሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የአዲሱ የአውሮፓ ትውልድ መለያና መሰየሚያ ሆነዋል።
ይህ የሆነው በስደተኞች ምክንያት ነው ብላችሁ ትሸወዱ ይሆናል። እንዲያ ከሆነ መልሱ አይደለም ነው። ፒው የጥናት ማእከልን ጨምሮ በርካታ ተቋማት እንደሚያሳዩት ከሆነ በአውሮፓ እያደገ ከመጣው የኢስላም ቁጥር ከግማሽ በላዩን የአውሮፓ ተወላጆች ይይዛሉ።

አውሮፓ ነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የሚያንቋሽሹ ኢስላም ጠሎች ማእከል ነበረች።ያ ጥላቻ በተስፋፋ ቁጥር Open minded ለሆነው የአውሮፓ ህዝብ ስለነብያችን የበለጠ እንዲያውቅና እንዲያነብ አድርጎታል

አሁን ላይ ነብያችን በአውሮፓ ቁጥር አንድ ተወዳጅ ሰው ናቸው።
የአውሮፓ ታላላቅ ዋና ከተሞች ከሚወለዱት ልጆች በመሰየም ሙሀመድ ቁጥር አንድ ስም ነው። ከነዚህም መካከል
👉 የጀርመኗ ዋና ከተማ በርሊን
👉 የእንግሊዝ ዋና ከተማ ሎንደን
👉 የኔዘርላንድ ዋና ከተማ አምስተርዳም
👉 የኔዘርላንድ ግዙፏ ከተማና የአለም ድፕሎማሲ መድና ዘሄግ
👉 የቤልጅየም ዋና ከተማና የአውሮፓ ህብረት ዋና መቀመጫ ብራስልስ
👉 የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎው
👉 የእግሊዟ ማንችስተር ይገኙበታል።

ነገሩ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እንዳለው ነው
" አውሮፓ በዚሁ ከቀጠለች የኢስላም አህጉር ትሆናለች"

የሙሀመድ ጠላቶች ይህንን እያዩ ቅጥል እያሉ ነው።ግና እንደቀድሞው ማንቋሸሽ አይችሉም።

ታዲያ ያሀበሻ ሙሂቦቻቼው
"ያረሱላሏሂ ስምሁ መጣፈጡ
ወተት እንደጠጡ ማር እንዳላመጡ
የማርስ ጥፍጥና ከከንፈር ይቀራል
ያንቱ ውዴታ ግን ሆድ ይበረብራል"
ብሎ ያንጎራጎሩላቸው

t.me/Seidsocial
❤135👍4🥰2🤔1
September 8, 2026 2.3K 15 12