ሕይወቴን ያደፈረሰው ምስጢር! ክፍል 18 በማግስቱ ጠዋት እናቴ በሩን ስትከፍት በደጃፋችን ላይ የታረደ ጥቁር… — 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿 — TG.ME

ሕይወቴን ያደፈረሰው ምስጢር!

ክፍል 18
በማግስቱ ጠዋት እናቴ በሩን ስትከፍት በደጃፋችን ላይ የታረደ ጥቁር ዶሮና ደሙ የተረጨበት ጨርቅ አገኘች። እናቴ በጮኸች ጊዜ አባቴና እኔ በፍጥነት ወጣን። ዶሮው አንገቱ ተቆርጦ በበራችን አቅራቢያ ተጥሎ ነበር ደሙም በመሬቱ ላይ ደርቆ ነበር።
አባቴ ነገሩን ሲመለከት በቁጣ ተሞላ። «ማን ነው እንዲህ የሚያደርግብን?! ማን ነው ቤታችንን ለማፍረስ የሚታገለው?!» ብሎ ጮኸ። የመንደሩ ሰዎች የ አባቴን ጩኸት ሰምተው በርቀት ቆመው ይመለከቱ ነበር፡፡ ወደኛም ሮጠው መጥተው የተገረሙም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ሊረዳን አልሞከረም አፉን በነጠላው ሸፍኖ ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ።
እኔ ያን ጥቁር ዶሮ ስመለከት በሰውነቴ ላይ ከባድ መንቀጥቀጥ ተከሰተ። አእምሮዬ ውስጥ አንድ ምስል መጣ ያ በዛፉ ስር ያየሁት የተቀበረ ነገርና ያቺ አሮጊት ። «ምናልባት እሳቸው ናቸው?» ብዬ አሰብኩ።
አባቴ እንጨት አምጥቶ ዶሮውንና ጨርቁን ወደ እሳት ጣለው። ነገር ግን ያን ነገር በእሳት ሲያቃጥለው በክፍሌ ውስጥ ከባድ የጭስና የኮሽኮሽ ድምፅ ተሰማ። በውስጤ ያለው ሕመም በእጥፍ አደገ አየር ማግኘት አቅቶኝ መሬት ላይ ወደቅኩ...
በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ አባቴና እናቴ ወደ እርሻው አካባቢ ሄደው ሳሉ እኔ በደከመ እግሬ ከቤት ወጥቼ ወደ አሮጊቷ ቤት አመራሁ። እውነቱን ማወቅ ፈለግኩ ለምን በእኛ ላይ እንዲህ እንደሚደረግ መጠየቅ ፈለግኩ።
ወደ እሳቸው ትንሽ አጥር ስቃረብ ሴቲቱ ገቢያቸው ስር በደጃፋቸው ተቀምጠው ቡና ይቆሉ ነበር። እኔን ሲመለከቱኝ አልደነገጡም ይልቁንም በጥልቀት እየተመለከቱኝ «መጣሽ?» አሉ።
እኔም እየተንቀጠቀጥኩ «እማማ ማዘር... ለምን በእኛ ላይ እንዲህ ያደርጋሉ? እኛ ምን በደልንዎት?» ብዬ ጠየቅኳቸው። ሴትየዋ የቆሉትን ቡና ከእሳቱ ላይ አውርደው «እኔ በእናንተ ላይ ምንም አላደረግኩም ልጄ ነገር ግን በዙሪያሽ ያለው ጨለማ እጅግ ትልቅ ነው። የሚጎዳሽ ሰው ከውጭ አይደለም... ከቅርብሽ ነው» አሉ።
የእሳቸው ንግግር ይበልጥ ደሜን አቀዘቀዘው። «ከቅርቤ? ማን ነው?» ብዬ ጠየቅኳቸው። ሴትየዋ ግን ከዛ በበለጠ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም። «ከዚህ በላይ ምንም አልናገርም ወደ ቤትሽ ተመለሺና አላህን ጠይቂ ፈጣሪያቹን ለምኚ» አሉ።
ብላቸው ብሰራቸው ብለምናቸው ብማፀናቸው እንደውም ቁጣ በተቀላቀለ ትዛዝ ከግቢያቸው አስወጡኝ፡፡
ወደ ቤት ስመለስ አእምሮዬ በብዙ ጥያቄዎች ተሞልቶ ነበር። «ከቅርቤ ያለው ሰው ማን ሊሆን ይችላል? ጎረቤቴ? ጓደኛዬ? ወይንስ ከቤተሰቤ አንዱ?» ብዬ መጠራጠር ጀመርኩ። ያ ጥርጣሬ አእምሮዬን ሊበታተነው ተቃረበ...


#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ

🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸

💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡

💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇

⭐️     https://t.me/Qallbdoc


ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇

https://t.me/UstazulQallb

👆

ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

📱 https://qalebdoctor.com
❤14
September 5, 2026 892 1 3