ከአቡ አዩብ አል-አንሷሪ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተዘገበው፣ ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
"ዊትር እውነተኛ እና የተደነገገ ሱና ነው። የፈለገ በሰባት ረከዓ ዊትር ይስገድ፣ የፈለገ በአምስት፣ የፈለገ በሦስት፣ የፈለገም በአንድ ረከዓ ይስገድ።"
(ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ እና ኢብን ማጃህ ዘግበውታል።)
ትምህርቱ፦
የዊትር ሰላት በጣም የተጠናከረ ሱና ነው።
የዊትር ረከዓዎች ቁጥር ላይ ሰፊ ምርጫ አለ፤ 1፣ 3፣ 5 ወይም 7 ረከዓ ሊሰገድ ይችላል።
ሁሉም በተረጋገጠ ሱና ውስጥ የገቡ መንገዶች ናቸው።
⭐️ https://t.me/Qallbdoc
✨https://t.me/dr_of_heart
