መረጃ ዘመደመር: post #70433 — TG.ME

አሜሪካ የ200,000 ሰዎችን ቪዛ ልትሰርዝ ነው

​የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በታሪክ ትልቁን የቪዛ ስረዛ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

እርምጃው በንግድ (B1) እና በቱሪዝም (B2) ቪዛ ወደ አሜሪካ ገብተው የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ወይም በመጠየቅ ላይ ያሉ እስከ 200,000 የሚደርሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን ዓላማ ያደረገ ነው።

​የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ከ2016 እስከ 2026 የተሰጡ ቪዛዎችን ለመሰረዝ ዝግጅቱን አጠናቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንደተናገሩት፣ እርምጃው ለአጭር ጊዜ ጉብኝት መጥተው ቪዛውን ለቋሚ መኖሪያነት የተጠቀሙበትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተወሰደ ነው።

​ይህ የቪዛ ስረዛ ሰዎች ወዲያውኑ ከሀገር እንዲወጡ ባያደርግም፣ ህጋዊ የጉዞ ሁኔታቸውን የሚያሳጣ በመሆኑ ከፍተኛ የህግ ክስና ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይገመታል።

የትራምፕ አስተዳደር ከዚህ ቀደምም በቪዛ አመልካቾች ላይ በርካታ ጠንካራ ገደቦችን ሲጥል መቆየቱ ይታወቃል።
August 25, 2026 33