በሕይወታችን ያሉ ጥሩ ሰዎችን በቀላሉ ለማጣት ከፈለግን . . .
1. መልካምነታቸውን መልመድ
ሰዎች የሚያደርጉልን በጎ ነገር፣ ፍቅር፣ ድጋፍና ታማኝነት ስንለምደው እና ምስጋና ማቅረብ ስንተው ሰዎቹን ቀስ በቀስ እናጣቸዋለን።
2. ለጥቅማችን ብቻ መፈለግ
እነሱን ከእኛ ጋር ስላላቸው ወዳጅነት ሳይሆን ጥቅም በምንፈልግበት ጊዜ ስንፈልጋቸው ሰዎቹን ቀስ በቀስ እናጣቸዋለን።
3. ደጋግመን መጉዳት እና አለመለወጥ
ስናጠፋቸው “ይቅርታ” እያልን ተመሳሳይ ነገር ደግመን በማድረግ ትዕግስታቸውን ስንፈታተነው ሰዎቹን ቀስ በቀስ እናጣቸዋለን።
4. እነሱን አለመስማት
የራሳችንን ሃሳብም ሆነ ስሜት እየገለጽን የእነሱን ስሜት ችላ የማለት፣ ንግግራቸውን የማቋረጥ ወይም ሁልጊዜ የራሳችንን ነገር ብቻ የማውራት ልማድ ካለብን ሰዎቹን ቀስ በቀስ እናጣቸዋለን።
5. ከጀርባቸው ስለ እነሱ ማውራት
ስለ እነሱ ሁኔታም ሆነ ተግባር ያለንን ሃሳብምና አመለካከት ከእነሱ ጋር መወያየት ሲገባን ከሌላ ሰው ጋር ስለ እነሱ ስናወራ፣ ምንም እንኳን ለጊዜው ቢታገሱንም ሰዎቹን ቀስ በቀስ እናጣቸዋለን።
በዚህ ምድር ላይ ሁል ጊዜ እንደሚገኝልንና እንደሚታገሰን ሰው አቅልለን የምናየው ነገር የለም፡፡ እነደዚህ አይነት ሰው ደግሞ የሚጠቅመንና የሚበጀን፣ አንዴ ካጣነው ደግሞ ደግመን ለማግኘት የሚያስቸግረን ነገር የለም፡፡
የሰዎች መልካምነትና ሁል ጊዜ መገኘት አይቅለልባችሁ
