ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ ተመርቆ ሥራ ጀመረ።
==========================
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በሆስፒታሉ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታል የዚህ አንዱ ማሳያ ነው አሉ።
ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው።
በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሃመድ ሳላህን በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን በማለት ተናግረዋል።
#ምንከማን
#minkeman
#Addisabab #Ethiopia
#Quality #Marketing
Telegram: t.me/minkeman
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL
Tiktok: tiktok.com/@minkemand
YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv














