ከየትኛውም አቅጣጫ ይነሳ…‼️
አላማቸው ከማይታወቅ ድብቅ ኃይሎች እና ከግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት ተፅዕኖ ያልተላቀቀ ስብስብ፣ አደረጃጀትም ቢሆን፣ ከፋሽስቱ ብልፅግና፣ ከብዐዴንስ በምን ይለያል?
በትግላችን ውስጥ፣ ተዋረዳዊ የስልጣን ደረጃን መጣኝ ሸፍጥ በፍረጃ እና በመጠፋፋት ላይ የቆመ በሴራ እና ተንኮል የታጀለ ፋሽስታዊ ግብረ ልምምድ ቀስ በቀስ በእግሩ ሲሄድ እየታየን ነው።
የፋሽስቱ ብልፅግና እኩይ ማንነቱ "ስረ ውል" ዋና ችግርኮ የአብይ አህመድ በዘረኝነት የተሳከረ፣ በሸፍጥ እና ሴራ የበለፀገ ለፍቅረ ስልጣን ህሊናው የታወረ ፈላጭ ቆራጭነት ነው።
በዚህ ወቅት…ገና ከቁጥቋጦ እና ምሽግ ሳንወጣ፣ ከሞት ጋር የሰዓታት ቀጠሮ ይዘን በምንዋደቅበት መራራ ሰልፍ ላይ ቆመን… ጉዳዬ ዋና ያደረግናቸው አጀንዳዎቻችን የሚያብራሩልን ቁም ነገሮች አስደንጋጭ ናቸው።
ሁሉም እንቶፈንቶ መቧቀሻ እና መዳቆሻ አጀንዳዎቻችን… የአሸናፊነታችንን ቅድመ ትንበያ እውንነት አያስረግጡም፣ አያፀድቁምም።
#ግለሰቦችን የነብይነት በትር አስጨብጦ የነፃነት መንገድ ተላሚ አድርጎ ተክለ ስብዕናን አጋኖ በመካብ ትይዩ…
ሌላኛውን ግለሰብ ደግሞ በተቃርኖ በትግል ደንቃራነት አግዝፎ ማጠልሸት እና የማሰይጠን… "#አርካሽ እና ቀዳሽ" መንገዳችን የሚጠቁመን አንድ መራራ ኃቅ ነው።
ገና፣ በአንድ መስመረ አምሓራዊነት የሚራመድ ጠንካራ ድርጅት ማዋለድ እንዳቃተን!
በጠንካራ ርዕይ የሚመራ እና በመርህ የተጠረነፉ መሪ እና ተመሪ ያለው ድርጅት ሲወለድ… ቅድመ ወሊድ የነበሩ አሉባልታዊ፣ በፍጭት ትርምስ ውስጥ ላይ ሳለን የሚታይብን ተፈጥሯዊ ውስጣዊ ህመሞች፣ ድህረ ወሊደ !#አምሓራ ድርጅት" ሁሉም በምስራች ተስፋ ቃል ይተካሉ። በድርጅታችን እድገት እና አላማዊ ተልዕኮ ስኬት ላይ ያተኮረ አጀንዳ እና ውይይት አየሩን ይይዛል። ለድርጅታዊ ራዕያችን መሳካት የሚሆኑን ሁነኛ ራዕይ የታጠቁ፣ የነቁ እና የበቁ መሪዎች እና ተመሪዎች በድርጅቱ አላማ እየተጠመቁ ለድርጅቱ ራዕዬ ስኬት በአሳዳጊነት በተዋረድ በየቦታቸው ይሰለፋሉ።
ዛሬ ላይ… በአንድ አላማ የምንሰለፍለት አንድ አምሓራዊ ድርጅት ለማዋለድ ያቃታቸው፣ የማይሹም፣ ነፃ ጀርባ የሌላቸው በአባታቸው አፋሪ፣ በምላሳቸው ታፋሪ ድቃይ በቅሎ ዲስኩረኞች… የትግላችንን ዓምደ ማዕከል ይዘው… አምሓራዊ መናኝ ጀግኖቻችንን ተስፋ ቢስ ሽብርክ እያደረጉ ነው።
ይህ፣ ያለፉ 2 ዓመታት የተፈተነ ለጠላት ጥቅም ያዘነበለ ጥራት አልባ መንገድ "#በቃ!" ሊባል ይገባል!
እንዴት⁉️
ይመለሳለሁ!
#Hiruy Amhara
#ቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችንን join አድርጉ።
#ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418
10/06/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
አዲስ አበባ
https://t.me/Moamediamor




