ይህ ዓለም በብዙ ሸክም ውጥረትና ጭንቀት የተሞላ ነው ብዙ ጊዜ የራሳችንን ችግሮች በራሳችን አቅም ለመሸከም ስንሞክር እንዝላለን ጌታችን ክርስቶስ ግን ዛሬ የሚጋብዘን ወደ እርሱ እንድንመጣና እውነተኛ እረፍትን እንድንወስድ ነው የእርሱ እረፍት ጊዜያዊ ሳይሆን የውስጥ ነፍሳችንን የሚያሳርፍ ሰላም ነው
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።" — ማቴዎስ 11:28-30

