እንኳን ፡ ለአበው ፡ ቅዱሳን ፡ አብርሃም: ፡ ይስሐቅ ፡ እና ፡ ያዕቆብ ፡ ዓመታዊ ፡ የዕረፍት ፡ በዓል ፡… — ኩራዝ — TG.ME

እንኳን ፡ ለአበው ፡ ቅዱሳን ፡ አብርሃም: ፡ ይስሐቅ ፡ እና ፡ ያዕቆብ ፡ ዓመታዊ ፡ የዕረፍት ፡ በዓል ፡ በሰላም ፡ አደረሳችሁ፤ ፡ አደረሰን። ፡ †††
†††በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አሐዱ ፡ አምላክ ፡ አሜን! ፡ †††
††† እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::

††† ቅዱስ አብርሃም ርዕሰ አበው †††

††† የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::

በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ:: "አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ:: መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን አልጠይቀውም?" በሚል አናገረው::

"እርቦኛል አብላኝ?" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ አጠጣኝ?" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ አጫውተኝ?" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዓይን እያለው የማያይ: ጆሮ እያለው የማይሰማ አምላክ የሚገዛ?" እያለ ይጮህ ጀመር::

ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል::" ብለውት ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ አብርሃም እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ የተፈጠርክ ዕፅ ነህ::" ብሎ ሰባበረው::

ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው:: የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ አባታችን አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ ከነዓን ከወጣ በኋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ ምክንያት ከአንድም ሁለት ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::

ሁለቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: ነቢይ ነውና በአብርሃም ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኳን ሠርቶ እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይዝም እህል አይቀምስም ነበር::

ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለሦስት ቀናት ቆይቷል:: በፍጻሜውም ሥላሴ በእንግድነት መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ: በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ ይስሐቅን አብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::

አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት: የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት: ሥርወ ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል:: ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::

አንድ ቀን እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም አለ::" አላቸው:: ያን ጊዜ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
*"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው::) እያሉ አሰምተው ተናግረዋል::

አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ ተጠቅሷል:: ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም በሲዖል ውስጥ እንኳ ማረፊያን ሠርቶለታል:: አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም ከክርስቶስ ልደት አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት ነው:: እድሜውም መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ (ድንኳኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ አመስግነዋታል::
ሊቁም:-
††† "አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር ገልጾታል::

††† ቅዱስ ይስሐቅ ርዕሰ አበው †††

††† የደግ ዛፍ ፍሬ: የአብርሃም ልጅ ደጉ ይስሐቅ እጅግ ንጹሕ በመሆኑ የወልድ ክርስቶስ ምሳሌ ተብሏል:: የይስሐቅ ልደት እጅግ የተጠበቀ ከመሆኑ ባሻገር የተፈጸመውም በብሥራተ አምላክ ነው:: ስሙንም ያወጡለት ሥላሴ ናቸው:: ቡሩክ ይስሐቅ በብዙ ነገሩ ድንቅ ነው::

ለእርሱ ሃያ ዓመት ለአባቱ መቶ ሃያ ዓመት በሆናቸው ጊዜ ጭንቅ ትዕዛዝ ከፈጣሪ ዘንድ ተሰማ:: አብርሃም ይሰዋው ዘንድ ወደ ደብረ ምሥጢር ይዞት ከወጣ በኋላ መስዋዕቱ እርሱ እንደ ሆነ አወቀ:: ለፈጣሪውና ለአባቱ ይታዘዝ ዘንድ "እሺ" አለ::

በዚያውም ላይ አባቱን "አባ ስንፈራገጥ እንዳልጐዳህ እሠረኝ:: ዓይኔን አይተህ እንዳትራራ በሆዴ አስተኛኝ::" አለው::

አቤት ትሕትና! አቤት መታዘዝ! ወዮ አባታችን ይስሐቅ! ቅንነትህ ምን ይደንቅ! ለዚህ አነጋገርህ አንክሮ ይገባል!

††† "ሰላም ለይስሐቅ ዘኢያግዘፈ ክሳዶ:
ለደኒን ወለተሐርዶ"
እንዲል::

ቸር ፈጣሪ ግን የአብርሃምን አምልኮ: የይስሐቅን ንጹሕ መታዘዝ ለዓለም ገለጠ እንጂ እንዲሞት አላደረገም:: ቅዱስ ይስሐቅ በዚህች ዓለም ለመቶ ሰማንያ ዓመታት: በትዳር ደግሞ ለመቶ ሃያ ዓመታት ቆይቷል:: ከቅድስናው የተነሳ በእነዚህ ጊዜያት ከአንድ ቀን በቀር ከሚስቱ ርብቃ ጋር አልተኛም:: በዚህቺው ዕለትም ያዕቆብና ኤሳው ተጸንሰዋል::

እግዚአብሔር በመቶ ሰማንያ ዓመቱ ወደ ሰማይ ይዞት ወጣ:: በዚያም ግሩም ምሥጢርን ተመለከተ:: በእሳት መጋረጃ መካከል አብርሃምን አየው:: ከአምላክ ዙፋንም እንዲህ የሚል ቃል ወጣ::
*"ወዳጄን ይስሐቅን የሚያከብረውን አከብረዋለሁ::
*ልጁን አምኖ "ይስሐቅ" ብሎ የሚጠራውን
*በስሙ ለነዳያን የሚራራውን
*ለቤቱ እጣን ያመጣውን
*በዚህች ሌሊት በጸሎት የተጋውን
*'አምላከ ይስሐቅ' እያለ መቶ (100) ጊዜ የሰገደውን
*ዜና ይስሐቅን የጻፈውን: ያነበበውን ሁሉ በመንግስተ ሰማያት ዋጋውን እከፍለዋለሁ::

ይህንንም ልጁ (አባታችን ያዕቆብ) ተመልክቶ ከትቦታል:: ቅዱስ ይስሐቅም ከንጽሕናው ሳይጐድል በበረከት እንዳጌጠ ዐርፏል::
❤6
September 2, 2026 222 1