ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ🤔
ነገወር በገባ በ29 ታስባ የምትውለው እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ናት
📚 ያደረገችው ታዕምር ይህ ነው ፡እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶሰ የተወለደችው በጎንደር ክፍለ ሀገር በደራፎገራ አንበሳ መዳ ነው፡፡
የተወለደችው ክርስቶስ በተወለደበት ቀን ታኅሣሥ 29ቀን በመልአከ አብሳሪነት ተወለደች፡፡
በተወለደችም ጊዜ በእግሯ ቆማ ከጨለማ ወደ ብርሐን ላወጣህኝ ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅድስ ምስጋና ይገባል ብላ አመሰግናለች፡፡
እርሷ በነበረችበት ዘመን ንጉስ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ"የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት ሕዝቡ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በሀገራችን
ከፈተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ሰለተነሣ ከ8ሺ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲየልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖን እና ከሌሎችም ቅድሳን ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነት ዐርፋ ሰባት አክሊልን ወርዶላታል፡፡
ቅድስት እናታችን አምላኳን እሰከ ሐጨረሻው በድንግልና መገልገል ብትፈልግም ዕድሜዋ ለ ከፍ ሲል ቤተሰቦቿ ዘርዓ ክርስቶስ ከሚባል አገረ ገዥ ጋር አጋባት፡፡ እርሷም ግን በጫጉላ ቤት እያሉ በእኩ ሌሊት ቧሏን ወንድሜ ሆይ
እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ ነገር ድንግልናችንን እጠብቅ አለችው እርሱም እሺ አላት ይህን ተመካክረው በጸሎት ሲተጉ አደሩ፡፡ በሌሊትም ወደ ባሕር ውስጥ እየገቡ ጸሎት ያደርጉ ጀመር፡፡
በመጨረሻም እርሷ በጳጳሱ በአባ ማርቆስ እጅ ስትመነኩስ ቧሏም ድንግልናውን እንደጠበቀ በሰማዕትነት አንገቱን ተሰይፎ ዐርፏል፡፡
መልአኩም ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኃላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ሴትደርስ ከቦታዋ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ በቀሰተ ደመና ተከቦ አይታ ይህቺ ቦታ ምንታምር ብላ ጠራቻት፡፡ በቦታውም ላይ በመድኃኔ ዓለም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታለች፡፡
እናታችን ቅድስ ፍቅርተ ክርስቶስ የሠራቻት በሰሚዝ(በሰንሰል)እንጨት በአይጥ ሐረግ፤ በነጠላ ማገር አድርጋ የግድግዳ ቤተ መቅደስ በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታ በታህሳስ 16ቀን በዕለተ እሁድ አሰቀድሳለች፡፡
ቅዱስ ሩፉኤልም መሲፋይልም በክንፋቸው አፈር ከእየሩሳሌም አምጥተው በቦታዋ ላይ ቀላቅለውበታል፡፡
፼ጌታችንም ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ተገልጦላት ቦታዋን ባርኮላታል፡፡ ☞ቤተ ክርስቲያኗ አስከ እለተ ምጽአት እንደማትፈርስ ቃል ገብቶላታል፡፡
ይቺ ቤተክርስቲያን ጌታችን ለቅድስ ፍቅርተ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሊሰጣት ሲመጣ ሰግዳለች፡፡ዛሬም በአራቱ አቅጣጫ ሲመለከቱት ዘንበል ብሎ ይታያል፡፡
የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ያደረገችው ታዕምር ይህ ነው፡፡
በሀገሯ አቅራቢያ የሚኖሮ አንድ አይነ ስውር ነበር፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን እጅ ይነሣ ዘንድ በዛው በአይኖ መታወር ሁሌ ያዝ ነበር እና እንድታማልደው እናታችን ቅድስት ፍቅርቶስን ለመለመን ሄደ፡፡
በዚየም ቆሞ ሲጸልይ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እንባዋን እንደ ውሃ እረጨችው፡፡ በዚያን ጊዜ አይኖቹ በሩለት እና እየ በፊቷም ሰገደ፡፡
እስከለተ ሞቴ ድረስ ለሰው አትንገር አለችው ይህን ብላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ተሰወረች፡፡
የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡
የእናታችን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡ የዕረፍቷም
መታሰቢያ የካቲት 29 ቀን ነው፡፡ የዛ ሰው ትበለን፡፡
3September 3, 2026 198