ወዳጆቼ! አምላካችን እኛን የሚወድበት ፍቅር ከማንኛውም ምድራዊ ወላጅ ፍቅር እጅግ ይበልጣል። ኃጢአታችን ምንም… — ኩራዝ — TG.ME

ወዳጆቼ! አምላካችን እኛን የሚወድበት ፍቅር ከማንኛውም ምድራዊ ወላጅ ፍቅር እጅግ ይበልጣል። ኃጢአታችን ምንም ያህል ቢበዛ፣ የእርሱ የምሕረት ባሕር ከኃጢአታችን ታላቅነት በላይ ነው። የባሕር ውኃ አንዲትን የቆሻሻ ጠብታ አጥልቆ እንደሚያጠፋት ሁሉ፣ የእግዚአብሔርም ቸርነት በንስሐ የሚቀርበውን ሰው በደል ሙሉ በሙሉ ያጥባታል። በየትኛውም የኃጢአት ማዕበል ውስጥ ብንሆንም በፍቅር ወደ እርሱ እንምጣ፣ አምላካችን ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኛን አይጠላምና። ✍️ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!       ነሐሴ 27, 2018 ዓ.ም

September 2, 2026 208 3