JOHN TUTORIAL 🧑‍💻: post #2874 — TG.ME

❇️ዩኒቨርስቲ_ገነት_አይደለም‼️

የከርታታው_መምህር_መልእክት

Abebayehu Geta Enaro (Msc)

✳️CGPA 3.94

❇️HAWASSA UNIVERSITY

https://t.me/Johnastu/5582

👆🙏 ከስር ያያዝኩት የ #Masters_Degreeዬ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።

🙏 በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።

🙏 በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ እና በተለያዩ የሙያ የንግድ እና የመሳሰሉ ነገሮች ላይ የተሰማሩ በአሁኑ ሰዓት የቤት አከራዮቼ ናቸው ፤ ባለመኪና ባለሆቴል ጽድት ያለ ቡቲክ ብቻ ምን አለፋህ በአጠቃላይ ከእኔ እጅግ በጣም በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ነው የሚገኙት!😭

🙏 በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪ የያዘ የዩኒቨርስቲ መምህር የሚከፈለው ደመውዝ ግብር ሳይቀነስ 12,579 ብር ነው ፤ 35% ግብር እንዲሁ የጡረታ ሲወጣ ኪሴ የሚገባው 9956(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት)ብር ነው።

🙏 እንግዲህ በትምህርት ደረጃዬ ሲወራልኝ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ ፤ ሶስተኛ ድግሪዬን ብሰራ እና ዶ/ር አበባየሁ ጌታ ብባል ወደ 16,000 ብር ከታክስ በፊት እና ወደ 13,000 ብር ገደማ ከታክስ በኋላ እጄ ላይ ይደርሳል።

እና ለምንህ ነው ዩኒቨርስቲ ቀረብኝ ብለህ የምትጨነቀው?

ወዳጄ/ወንድሜ/እህቴ 12 ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አልመጣልህም?

✳️እሰይ እንኳንም አልመጣልህም!

🅾ራስህን ለመቀየር ታትር ፣

❇️አጫጭር ኮርሶችን ከዩቲዩቭ አውርድ ፣

⛔️ተማር ፣ቪዲዮ ቱቶሪያል ተከታተል ፣
ግራፊክስ እና

❇️የመሳሰሉ ገንዘብ ልትሰራ የምትችልባቸው ከምርጥ ኮንተንት ጋር ከመጣህ የዩቲዩብ ስራዎች, ብቻ ብዙ ብዙ አማራጮች አሉህ፣
ተስፋ አትቁረጥ! 👇👇👇👇👇👇👇

‼️በበሰበሰ ስረዓተ ትምህርት ብዙ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ባልወሰዱበት ከስር ተጀምሮ ባልተሰራ ስራ እና ሰረዓት ተምረህ መጥተህ መጨረሻ ላይ ብትወድቅ(የመስዋዕት በግ ብትሆን) ብቻህን ተጠያቂ አይደለህም! 🤨

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

✳️ራስህን ብቻ አትውቀስ! እልፍ በል! ታገል! እመነኝ ታመሰግነኛለህ!🙏‼️

🛑 Via ሸገር ታይምስ /2023 GC/

⤵️⤴️⤴️ ‼️ Share ‼️⤴️⤴️⤴️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 
🔥Youtube ቻናላችንን Subscribe በማረግ
ትምህርታዊ መረጃዎችን በቪዲዮ ያግኙ
እንዲሁም የ Online ስራዎች ያገኙበታል
👇👇......👇👇......👇👇......👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 
https://youtu.be/L8LCdhB9AXA?si=1HOOoohMemdmdIUX
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
❇️ በየቀኑ ጠቃሚ መረጃ
         .. ...እንዲደርስዎ ይቀላቀሉን 👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
   ⬇️Join and Share⤴️ FOR MORE👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 
         ♦️  
@John_Tutorial   ❇️
         ♦️  
@John_Tutorial   ❇️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 
💬 Discussion 👉
@Johnastu
📖 Digital Library 👉
@JohnLibrary
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
❤6👏5👍4🔥3🥰2
August 28, 2026 1.3K 21