ማፍላት እና መብረድ (ድጌ) ============= የሆነ ጊዜ ቴኳንዶ ገብቼ ደህና መወራጨት ጀመርኩ:: ሒሳብ… — Hasen Injamo — TG.ME

ማፍላት እና መብረድ
(ድጌ)
=============
የሆነ ጊዜ ቴኳንዶ ገብቼ ደህና መወራጨት ጀመርኩ:: ሒሳብ ከምሠራለት የሕንጻ መሳሪያ የሚያምር ጉርድ Safety-shoes ገዛሁ:: ጫማው ከፊት ብረት ስላለው በቴኳንዶኛ ስንዘራ ማንንም ብትመታበት ይወድቃል:: ይህንን ፍላቴን በማን እንደማበርደው ግራ ገባኝ:: የሚለክፈኝ አጣሁ:: ዝም ብለው የቆሙ የስልክ እንጨቶችን በሴፍቲሹ (ጫማ) እቺን ለቁመትህ ... ይህንን ለገመድህ እያልኩኝ ወዝውዤው ሥራ እሄዳለሁ:: ሥራም ላይ ሲያወሩ ንግግሩ የነገር ነው ወይስ አይደለም እላለሁ:: ብቻ ወበራሁ:: አፈላሁ:: ችግር ግን አላደረስኩም::

ከዕለታት ባንዱ የተባረከ ቀን ይመስለኛል እንደ ልማዴ አዳራሽ ገባሁ:: ሳቦም ገበየሁ አረፈደ:: እኛ አሟሙቀን እስኪመጣ ካገኘነው ጋር ፋይት ጀመርን:: እኔ ከቀጫጫዋ ሶፊያ ጋር ልሞክራት አልኩ:: በቤልት ደረጃ እንራራቃለን:: ያው ቀጫጫ ስለሆነች በዚያውም ነገር ለመፈለግም ለመተዋወቅም ሰበብ ይሆናል በሚል ፋይት ጋበዝኳት:: ወንድሜ ምናለ ውጪ ክትፎ ብጋብዛት! እግሯ ከላይ በግሮሊጊ ሲወርድ እኔ ደግሞ ከስር ሰላም ለማውረድ አሰላሙዓለይኩም አልኳት:: እሷም ስቃ ዋዓለይኩሙሰላም ብላ በቦክሲኛ ይሁን በቴኪኛ አስተቃቀፍ ዓይነት ተቃቀፍን:: አጋጣሚውን ለመጠቀም እንተዋወቅ ስላት ዘወር ብላ ጠፋች:: ብዞር አጣሗት:: ከፍራክሽን ሰከንዶች እረፍት ግን እግሯ ከሗላ በዲቻጊ አገኘኝ:: ቦታው የፋይት በመሆኑ ጋባዥም እኔ ስለሆንኩ የሞት ሽረት ከአታክ ወደ ብሎክ ዞርኩ::

በዚሁ መሃል የቀበሌው ሰፊ አዳራሽ ሲከፈት ሳቦም ገበየሁ የመጣ መሰለኝ:: ግን ተለቅ ኮስመን ያለ ሰውዬ ገባ:: አብረውን ሕጻናትም ነበሩ:: እየሄዱ ተጠመጠሙበት (ባቸው):: እኔ ደግሞ ምን የሰው ፍቅር ያላቸው የቀበሌው ዘበኛ ናቸው ብዬ ወደ ሶፊ ፋይት ልመለስ ስል ወደ ፊት ወደ ብላክ ቤልት ረድፍ ሄዳ ተሰለፈች:: ሳቦም ገበየሁን ባየው የለም:: እኔ መሃል ረድፌ ላይ በቤልቴ ገባሁ:: የቅድሙ ኮስማና ሰውዬ መድረክ ላይ ሆኖ "ቺሪዮት" ሲሉ ምእመኑ ጸጥ አለ:: ዛሬ ደግሞ እዚሁ ስልጠናው ባደመጡ ዘበኛ ነው የምንሠራው ብዬ እስቲ ልያቸው አልኩና ምእመኑ ጋር አብሬ ኩኔ ገባሁ:: እዚያው መድረክ ላይ ያለች ትንሽዬ ግርዶሽ ገብቶ ለብሶ ቤልቱን ታጥቆ ወጣ:: ኢላሂ በሗላ ስሰማ ዋናው ማስተር ብርሃኑ ነው::

ቀጫጫዋ ሶፊ እንዲህ እንደ ሐረር ቃሪቦ ከጨለጠችኝ ... የማናቸው ሽሜ ያልኩትም ሰው እንዲህ ባለብዙ ዳን ሆኖ እንዲህ ከተገለባበጠ .. መንገድ ላይ ካለው ሰው ማን ነው የሚታመነው? ብዬ ማፍላቴ በርዶ በአደቤ ስልጠናዬን ቀጠልኩ:: እንደውም በሗላማ ፋይት ላይ ሳቦም "የእርሱን እግር ተጠንቀቁት, አንተም ቀንስ" ይለኝ ነበር:: ሳኮ-ፓድ ስንመታ ሲይዝልን የስንዘራ ፓወር ይለያል:: ብቻ ከዚያ ቀን በሗላ መንገድ ላይ ኮስማና ሰው ሳይ ባለስንት ዳን ይሆን? ቀጫጫ ሴት ሳይ ባለስንት ዳን ትሆን እያልኩ በአደብ አለሁ:: አንዳንዴ እረሳና እግሬ ይቀድመኛል እንጂ በብዙ ተሻሽያለሁ:: ሴዶ ስለሚባል ልጅ ሲወራ ማነው ብዬ ወደሗላ አንዳንድ ነገሩን ሳይ እኔም አንድ ሰሞን እንደዚያ አድርጎኝ ነበር አልኩ:: ይሁን:: ምን አገባኝ!

ቢዝነስ ላይ ስለትርፋማ ቢዝነስ ጤፍ ሲቆላ ካያችሁት አፍልቶ ነው:: ወይም ሿሿ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ ቢዝነስና ትርፋማነት ደፍረህ መናገር አትችልም:: እራስህ እየሠራኸው ስላለው ቢዝነስ እንኳ ደፍረህ በእርግጠኝነት መናገር አትችልም:: ዛሬ ላይ ስላለው ነገር ልታወራ ትችላለህ:: ከወር በሗላ ግን ብዙ ነገር ተቀይሯል:: ስለዚህ Main principles ከ A እስከ Z ይዘህ ግን ሁልጊዜ update መሆን ያስፈልጋል:: (ኢምፖርት ስለጠና እየሞላ ነው)::
❤12
September 8, 2026 1.1K 1