ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ! ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር… — ክርስቲያን ነኝ️️️ — TG.ME

ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ! ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል። በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡   ክርስቲያናዊ መረጃ በፍጥነት ➺በክርስቲያን ነኝ https://t.me/Gosepale

March 30, 2025 276