በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉም ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ።
*********
በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሁሉም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በተገኙበት ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል አዲስ አበባ ሆቴል ውይይት ተደረገ።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር ፍርድ ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጠናውን "የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ" ሪፖርት ሰነድን አስመልክቶ በተናገሩበት ወቅት ባለፋት አምስት የስትራቴጂክ ዕቅድ ዓመታት በውስንነት ከተለዮት ችግሮች አንዱ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መሆኑን በማስታወስ ፍርድ ቤቱ በ2018 በዕቅድ ከያዛቸው ስራዎች አንዱ የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ማከናወን መሆኑን አስገንዝበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸዉ የዳኝነት አገልግሎት ጥራትን ከሚያረጋግጡ ቁልፍ መሳሪያዎች አንዱ ተከታታይነት ያለው የድህረ-ውሣኔ ኦዲት ስራ መስራት መሆኑን በመግለፅ በተለይም ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ወጥነት ያለው አሠራርን ለማስፈን፣ የስልጠና ፍላጎትን ለመለየት፣ ተጠያቂነት እና ግልፅነት ለማስፈን፣ ክፍተቶችን ለይቶ ለማስተካከል እና የሕዝብ አመኔታ ለማግኘት የድህረ-ኦዲት ውሣኔ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
3August 3, 2026 2K 1




