የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court): post #2972 — TG.ME

በሰባት ምድብ ችሎቶች የኢ-ፋይሊንግ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የስካኒንግ ስልጠና
ተሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎቱን በማዘመን ቀልጣፋ፣ወጪ ቆጣቢ እና ተደራሽ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከልደታ እና ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎቶች በተጨማሪ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎቶች መዝገቦችን ስካን በማድረግ በዲጅታል ፎርማት ማስቀመጥ የተጀመረ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥራ ላይ የዋለውን የኢ-ፋይሊንግ ሲስተም በመጠቀም እነዚህ ምድብ ችሎቶች ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይግባኝ ስካን በማድረግ በኢፋይሊንግ ስሲተም በመላክ ላይ ይገኛሉ፡፡
❤1
August 28, 2026 346