🚨🇸🇩 የሱዳን ጦር ሚስጥራዊ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ማምረቻ እንዳለው የሚገልፁ መረጃዎች ይፋ ሆኑ፡፡ ዋሽንግተን ፖስትና ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጦች ዛሬ ባሰራጩት ዘገባ የሱዳን ጦር ሀይል ሚስጥራዊ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ ባከናወኑት ምርመራ ከመንግስታዊ ዶክመንቶች፣ ከተጠለፉ የስልክ ግንኙነቶችና ከስለላ ሰነዶች በመነሳት ይህ ፕሮግራም ተፈፃሚ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ሀይል ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ማስተባበያ የሰጠ ቢሆንም የጋዜጦቹ ዘገባ ግን የኬሚካል ጦር መሳሪያዎቹ እየተካሄደ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የሚገልፅ ነው፡፡ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባ እንደሚያስረዳው በዚህ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ማምረት ስራ ውስጥ በእርዳታ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች የቀረቡ ቁሳቁሶች ጭምር አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡
እንደምሳሌም ለህዝብ ውሀ ማጣሪያ ታስበው በእርዳታ የተሰጡ ፈሳሽ ክሎሪኖች የኬሚካል ጦር መሳሪያውን ለማምረት እንደዋሉ አስታውቋል፡፡ እንደዘገባው እነዚህን የጦር መሳሪያዎች ቢያንስ ሁለት ጊዜ ለመጠቀሙ የሚያሳዩ መረጃዎችም ተገኝተዋል፡፡ ይህ የኬሚካል ጦር መሳሪያው ጉዳይ ባለፉት አመታት ትልቅ ውዝግብ የፈጠረ ሲሆን አሜሪካ በዚህ የተነሳ በሌተና ጄኔራል አልብሩሀንና ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ላይ ማእቀብ መጣሏ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትና ከአሜሪካ ፋይናንስ ድርጅቶች ተጠቃሚ እንዳትሆን ገደብ ጥላለች፡፡
የአለም ፀረ ኪሚካል ጦር መሳሪያ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ግልፅና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረበ ቢሆንም የሱዳን መንግስት ግን መርማሪ ኮሚቴ መስርቶ የራሱን ማጣራት እያደረገ መሆኑን መግለፁ አይዘነጋም፡፡ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በዛሬ ዘገባው እንዳስታወቀው በአልብሩሀን በተመሰረተው ኮሚቴ ውስጥ ሊቀመንበር የሆኑት ግለሰብ በኬሚካል ጦር መሳሪያ ፕሮጀክቱ ውስጥ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ናቸው፡፡🕯🧯💈
ዘገበው ሆኑ፡፡ የ [ዋሽንግተን ፖስት እና ኒውዮርክ ታይምስ ]
.
.
.
ቴሌግራም፦
📌t.me/Brics4ethiopia
Forwarded fromBRICS 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
September 5, 2026 318 1