ለኢማሙ ሲሆን "ወራሪ"
ለአጼዎቹ ሲሆን "ሀገር ምስረታ"
.
.
ስህተታቹ የሚጀምረው
ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም ቢን ጋዚ (አህመድ ግራኝ) ያደረገውን ጦርነት "ወረራ"
እነ ምኒሊክ እና ሌሎች አጼዎች ያደረጉትን ደግሞ "ሀገር ምስረታ" በማለት መጥራት ስትጀምሩ ነው።
ኃላ ቀሩ እና እምነት ስር የተወሸቀው የፖለቲካ ግንብ ሊደረመስ ይገባል!!!
ከራሱ አመለካከት ውጭ ያሉትን ሁሉ እንደ እብድ ው* ሻ እየተናከሰ የኪሳራ ፖለቲካን በማራመድ በንጹሀን ህይወት የሚቆመረውን ሴራ እንዲቆም ሁላችንም በአንድ ድምጽ ልንነግራቸው ይገባል።
ከመነሻው መናገር ካስፈለገ
" ኢማም አህመድ ግራኝ ወራሪ አልነበሩም." አራት ነጥብ።
.
ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም ቢን ጋዚ ለአንድ ሺ አመት ገደማ በሙስሊሙ ላይ የተጫነውን የስቃይ ቀንበር ለጊዜውም ቢሆን ያሽቀነጠረ፥ የአምባገነን ነገስታት እብሪት የገደበ ታላቅ ጀብድ ሰርተው ያለፉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ንጉስ ናቸው።
እደግመዋለሁ። ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ናቸው።
.
የሀገሪቱን ታሪክ ለነሱ በሚስማማ ወርድና ቁመት የሚሰፉ የወቅቱ የ ታሪክ ጸሀፊያን የኢማም አህመድን ገጽታ እንደ ወራሪ እንደሳሉት ሳይሆን ከሌሎች ነገስታት የእሳቸው ታሪክ በጥላቻ ሲከተብ የተኖረው የተለየ ጥፋት ኖሮባቸው ሳይሆን ሙስሊም ሆነው በመፈጠራቸው ብቻ ነው ቅዋሜው!
በየዘመናቱ ተረማምዶ እስከ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ የዘለቀው ጸረ ሙስሊም ሸውራራ እይታ ዘመናዊ በተሰኘው ትውልድም ዛሬም የጥላቻ አሻራው እንዳለ ቅልብጭ ብሎ በመታየት ላይ ይገኛል:: ነገስታቱ ባይኖሩም ከአጥታቸው የዘለቀው የኢማም አህመድ ጥላቻ ጥርሳቸውን ባልነቀሉ የአሁን ትውልድ ላይም እናገኘዋለን::
ለዚህ ከምክንያቶች አንዱ ስለኢማሙ በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን፥ የትምህርት ተቋማት፣ ሀይ ባይ ባጣው ጥላቻን ባረገዙ የሚታተሙ መጽሀፎች ፣ አሁን ላይ በምንጠቀማቸው ሶሻል ሚድያዎች የሚንሸራሸረው የተሳሳተ መረጃ ነው::
.
ለአምስት ምእተ-አመታት የበቀለ የጥላቻ አረም በአጭር ጊዜ ማጨድ ቢከብድም፥ ከወዲሁ ቆርጦ "በቃ" በማለት ስራው መጀመር ይኖርበታል።
፡
እውነት መደበቅ የለበትም። የዚህችን ሀገር ታሪክ አንድ ቡድን እንደዘገበልን ሳይሆን፣ ዘመናዊ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የመሠረተውና የገዛው ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም ቢን ጋዚ (ግራኝ አህመድ ነው)። 15 ዓመት በጦርነት አራት ኣመት በሰላም ጎንደር ውስጥ ተቀምጦ አስተዳድሮዋል።
.
በአህመድ ግራኝ እና ልብነ ድንግል አመራርነት የተካሄደው የ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጦርነትም የእርስበእርስ ጦርነት እንጂ ወረራ አልነበረም፡፡(ወረራ ማለት ድንበር የተሻገረ የባእድ ሀይል ሀገርህን ለመቆጣጠር የሚያደርግብህ የጦርነት ዘመቻ ነው፡፡ለምሳሌ ኢጣልያ ያካሄደብንን ወረራ እንለዋለን )
.
ኢማም አህመድ ኢብራሂም ቢን ጋዚ (ግራኝ አህመድ ) ግን ከሌላ ሀገር ተነስቶ ኢትዮጵያን ያስገበረ ሳይሆን እንደማንኛው ነገስታት ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ እንደ ሌሎቹ ነገስታት በሀይል ያስገበረ ነው።
ስለዚህ ለኢማሙ ሲሆን "ወራሪ" ለአጼዎቹ ሲሆን "ሀገር ምስረታ" የምትለውን ስላቅ ገደብ ይበጅላት።
Via © Gumaa Saqqataa Gem ✍️
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
📌 t.me/Fastsinfo99
🌴 🌴 🌴
Telegram
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa.
✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን
✅|| write to us if you have any comments or complaints.
👀 @Fastmereja_Bot 👀

2September 5, 2026 438 2 2