አስቶን ቪላ ከአርሰናል - የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)… — FMC Sport ፋና ስፖርት — TG.ME

አስቶን ቪላ ከአርሰናል - የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የአምናው ሻምፒዮን አርሰናል ከሜዳው ውጭ አስቶን ቪላን ይገጥማል፡፡

መድፈኞቹ ኮቨንትሪ ሲቲን በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የጀመሩ ሲሆን፤ ባለሜዳው ቪላ በበኩሉ በብራይተን በሰፊ የግብ ልዩነት ሽንፈት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ድል የቀናቸው ሲሆን፤ በቀሪው አንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

ሁለቱን ቡድኖች የሚያገናኘው የሊጉ የሁለተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በቪላ ፓርክ ይደረጋል፡፡
👍1
August 31, 2026 2.3K 2