ፍቅር ላብ - Fkr Lab: post #696 — TG.ME

የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የየካቲት 17 2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፡_

❇️👉በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ብርሃኑ ፀጋዬ 83 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ጂቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ገለጹ፡፡

❇️👉ኢትዮጵያ በዚህ ወር መጨረሻ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ለማግኘት ወሳኝ ድርድር ልታደርግ መሆኑ ተሰማ፡፡

❇️👉የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ያቀረበ ሲሆን ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታው ነገ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቋል።

❇️👉የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ወደ 255 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ አለ፡፡

❇️👉የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ ውስጥ እንዲሰማራ በዛሬው እለት ከስምምነት መድረሳቸው የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

❇️👉በኢትዮጵያ የሚገኙ የሱዳን ስደተኞች ተጥሏል ባሉት ከፍተኛ የቪዛ ክፍያ ምክንያት ለችግር ተጋልጠናል አሉ፡፡

❇️👉የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚንስቴር ሰው ሰራሽ የገበያ እጥረትን ለመፍጠር ነዳጅን በህገወጥ መንገድ ጨለማን ተገን በማደረግና በችርቻሮ የሚሰራጩ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"
የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ዩቲዩብ፡-
https://www.youtube.com/@ebstvWorldwide/featured
👍10❤4🥰2
February 25, 2025 2.3K 2