ዓመታዊ የቤተሰብ ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዓመታዊ የቤተሰብ ቀን “ቤተሰብ ለሀገርና ለተቋም ግንባታ መሠረት ነው” በሚል መሪ ቃል የሠራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተሳተፉባቸው በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።
የአየር ኃይል የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ አርጋው፣ የቤተሰብ ቀን መከበሩ የአብሮነት፣ የመተሳሰብና የአንድነት መንፈስን ከማጠናከር ባለፈ ሀገራዊና ተቋማዊ እሴቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በዕለቱም ቤተሰቦች የአየር ኃይሉን የሥራ አካባቢና ተልዕኮ በተጨባጭ እንዲያውቁ የጉብኝት መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሠራዊት ቤተሰብ አባላት ለሆኑ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
በተያያዘ፣ የኢፌዴሪ አየር ኃይል 4ኛው አየር ምድብ “ትውልድን እናንፅ፣ ሀገርን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የወላጆች ቀንን አክብሯል። በዚህም በ2018 ዓ.ም በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሠራዊትና የሲቪል ሠራተኞች ልጆች የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ ተበርክቷል።
የ4ኛው አየር ምድብ ምክትል አዛዥ ለኤር ኦፕሬሽን ኮሎኔል አብይ ሀይሉ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረፅና የሀገርን ታሪክና እሴት በማስተማር የነገዋን ሀገር የሚረከብ ትውልድ የማፍራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል። ዘገባው የአየር ኃይል የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሪት ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
22
8
3September 6, 2026 3K 1