🇯🇵 የጃፓን መንግስት የ2027 የመጀመሪያ ዲግሪ (Undergraduate) ነፃ ትምህርት ዕድል ጥሪ
የጃፓን ትምህርት፣ ባህል፣ ስፖርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጃፓን በሚገኙ ታዋቂ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለመከታተል ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች የ2027 የትምህርት ዕድል ማመልከቻ መክፈቱን አስታውቋል።
የስኮላርሺፑ ጥቅሞች፡
✔️ ሙሉ የትምህርት ክፍያ፡ የማመልከቻ፣ የመግቢያ እና የትምህርት ክፍያዎችን ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል::
✔️ ወርሃዊ ድጎማ፡ ለተማሪዎች ወርሃዊ 117,000 የጃፓን የን (¥) የኪስ ክፍያ ይሰጣል።
✔️ የአየር መንገድ ትኬት፡ የደርሶ መልስ የኢኮኖሚ ክላስ የአየር መንገድ ትኬት ያካትታል።
✔️ የቋንቋ ስልጠና፡ መደበኛ ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ከፍተኛ የጃፓንኛ ቋንቋ ስልጠና ይሰጣል።
ይህ ዕድል ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ትምህርት እንዲቀስሙ ከመድረጉም በላይ፣ በጃፓን የሥራ ዕድሎችን ለማግኘትና ባህላዊ ልምዶችን ለመቅሰም ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው።
🔗 ሙሉ መረጃዎችን፣ መስፈርቶችን እና የማመልከቻ ቅጾችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/mext-undergraduate-scholarship-2027-in-japan-fully-funded/
ማሳሰቢያ፦ ማመልከቻው የሚከናወነው በኢትዮጵያ በሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ በኩል መሆኑን ተገንዝበው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

4
3May 4, 2026 1.6K 1 22