የቤልጂየም መንግስት የስኮላርሺፕ እድል ለኢትዮጵያውያን!
ለኢትዮጵያ ተማሪዎችና ባለሙያዎች፤ በእርግጥም ሊያመልጣችሁ የማይገባ አሪፍ እድል ነው።
የ2027-2028 የቤልጂየም መንግስት ስኮላርሺፕ በቤልጂየም ሀገር በልዩ ባለሙያነት የዲግሪ፣ የማስተርስ እና የሙያ ስልጠናዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ለመማር ያስችላል።
ምን ምን ይሸፍናል?
- የትራንስፖርት ወጪ
- ወርሃዊ የኑሮ አበል
- የትምህርት ክፍያ
- የጤና እና የህይወት መድን
- የቪዛ ወጪዎች
- በቆይታ ጊዜ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ
ኢትዮጵያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ናት።
የጥናት መስኮች:
- ሰብአዊ መብቶች (Human Rights)
- ዓለም አቀፍ እና የልማት ኢኮኖሚክስ (International & Development Economics)
- ማይክሮ ፋይናንስ (Microfinance)
- የህዝብ ጤና (Public Health)
- የምግብ ዋስትና (Food Safety)
- የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity)
- የአደጋ እና ስጋት አስተዳደር (Disaster & Risk Management)
- ዲጂታል አቅርቦት ሰንሰለት (Digital Supply Chain) እና ሌሎች ተጨማሪ መስኮች
የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት (የቤልጂየም ሰዓት አቆጣጠር)።
ሙሉ የትምህርት መስኮቹን፣ የማመልከቻ መስፈርቶችን፣ የሚጠየቁ ሰነዶችን እና የአመልካች አሰራር ሂደቱን አጠቃላይ መመሪያ አዘጋጅተንላችኋል።
ሙሉውን ጽሁፍ በEdMap website ላይ ያንብቡ፡ https://www.edmap.et/belgium-government-scholarships-20272028/

3
1August 14, 2026 637 1 23