🇯🇵የጃፓን መንግስት የ2027 የነፃ ትምህርት ዕድል (Master’s እና PhD ፕሮግራሞች )
የጃፓን መንግስት ለኢንተርናሽናል ተማሪዎች የሚሰጠውንና ሙሉ ወጪን የሚሸፍነውን ታዋቂ የነፃ ትምህርት ዕድል ይፋ አድርጓል።
ይህ የትምህርት ዕድል በጃፓን በሚገኙ የሁለተኛ ዲግሪ (Master’s) እና የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች የቀረበ ነው።
የስኮላርሺፑ ጥቅሞች፡
✔️ ሙሉ የትምህርት ክፍያ (Full Tuition Coverage)
✔️ ወርሃዊ የኑሮ ድጎማ (Monthly Stipend)
✔️ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት (Travel Expenses)
✔️ በጃፓን በታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የመማርና የምርምር ዕድል
ይህ የትምህርት ዕድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው ትምህርት ለመቅሰም እና በላቁ የምርምር ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ትልቅ አጋጣሚ ነው።
🔗 መስፈርቶችን ለማንበብ እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/mext-scholarship-2027-in-japan-fully-funded/
ማሳሰቢያ፦ ማመልከቻው የሚከናወነው በኢትዮጵያ በሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ በኩል መሆኑን ተገንዝበው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

May 4, 2026 1.1K 8