ጉዞ ወደ ሲንጋፖር ? የNUS Young Fellowship ዕድል ክፍት ሆኗል! 🇸🇬
በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው National University of Singapore (NUS) ውስጥ ለአንድ ወር የሚቆይ የFellowship ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ዋናው ነገር ደግሞ IELTS/TOEFL አይጠይቅም፣ የማመልከቻ ክፍያም (Application Fee) የለበትም!
✨ የፕሮግራሙ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?
🏨 ነፃ መኝታ: ሲንጋፖር በሚቆዩበት ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ነፃ መኝታ ይቀርባል።
💵 የኪስ ገንዘብ: ፕሮግራሙን ሲጨርሱ የ 500 SGD (የሲንጋፖር ዶላር) የጉዞ ድጎማ ይሰጥዎታል።
🤖 AI & Research: ስለ Artificial Intelligence እና ስለ ምርምር ከታዋቂ ፕሮፌሰሮች ጋር አብረው ይማራሉ።
🏙 ጉብኝት: እንደ Gardens by the Bay ያሉ የሲንጋፖር አስደናቂ ቦታዎችን የመጎብኘት ዕድል ይኖራችኋል።
ማን ማመልከት ይችላል?
- በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ (Major) ያለ የ3ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ።
- ጥሩ የትምህርት ውጤት ያለው።
- ከትምህርት ውጪ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች (Extra-curricular activities) ላይ የሚሳተፍ።
📅 ወሳኝ ቀናት:
የቆይታ ጊዜ: ከJune 22 እስከ July 24 ቀን 2026 (በአካል እና በኦንላይን)።
የማመልከቻ መጨረሻ: መጋቢት 15 ቀን 2026 (March 15, 2026)።
👇 ሙሉ መረጃውን እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ሊንክ ይጫኑ: https://www.edmap.et/the-nus-2026/

2
2January 2, 2026 2.4K 1 31