EdMap Community: post #1274 — TG.ME

🇹🇼 ታይዋን ICDF Scholarship- ሙሉ ወጪ የተሸፈነ የትምህርት ዕድል

የታይዋን ICDF Scholarship ምዝገባ መጀመሩን አብስሯል።

ይህ ስኮላርሺፕ በታይዋን በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በማስተርስ (Master’s) እና በዶክትሬት (PhD) ደረጃ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ለሚፈልጉ አመልካቾች ሙሉ ወጪን የሚሸፍን ዕድል ይሰጣል።

ተመራጭ የሚያደርጉት፦
🔹 ሙሉ ወጪ የተሸፈነ፦ ትምህርት ቤት፣ መኖሪያ፣ የጤና ኢንሹራንስ እና የመጽሐፍት ወጪዎችን ያካትታል።

🔹 የጉዞ ወጪ፦ የደርሶ መልስ አውሮፕላን ትኬት ይቀርባል።

🔹 ወርሃዊ ድጎማ (Stipend)፦ ለኑሮ ወጪ የሚሆን እስከ 20,000 NT$ በየወሩ ይከፈላል።

🔹 በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው 32 በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሚሰጡ ፕሮግራሞች (እንደ Engineering, MBA, Public Health, ICT) መማር ያስችላል።

የማመልከቻ መስፈርቶች፦

- የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው/ያላት።

- የሚመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠይቁትን የትምህርት ዝግጅት የሚያሟላ።

የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፦ March 15, 2026

የአመላለከቱን ሂደት፣ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን እና የትምህርት አይነቶችን ዝርዝር ለማግኘት ድህረ-ገጻችንን ይጎብኙ፦

🔗 https://www.edmap.et/taiwan-scholarship-2026/
❤7👍1
December 19, 2025 1.9K 26