ከ“አልችልም” ወደ “እችላለሁ”!
“አልችልም” የማለትን ሁኔታ ብዙ ሰዎች በአንደበታቸው አውጥተው ባይናገሩትም፣ በውስታቸው ግን ሲያብሰለስሉት ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በእድገታቸው ላይ ከፍተኛ ጫናን ያስከትላል፡፡ ስለሆነም፣ “አልችልም” ከማለት፣ በመውጣት ወደሚቻለው አመለካከት ለማለፍ አስፈላጊውን ግንዛቤና ልምምድ ማዳበር የግድ ነው፡፡
ከ“አልችልም” ወደ “እችላለሁ” የሚደረገው ጉዞ ቃላትን መቀየር ብቻ አይደለም። አስተሳሰብን፣ እምነትን፣ ዝግጅትን፣ ተግባርንና ጽናትን መቀየር ነው።
ተግባራዊ ልምምዶች:-
1. ጥያቄውን መቀየር
“ይህን ነገር አልችልም” ከማለት ይልቅ፣ “ይህን ነገር ለመቻል ምን መማር፣ ምን ማድረግና ምን መቀየር አለብኝ?” ወደሚለው መቀየር።
2. ዝንባሌን መቀየር
“አልችልም” የሚለውን አመለካከት፣ “እስካሁን አልቻልኩም” በሚለው በመቀየር ለራስ ተስፋን መስጠት እና ወደፊት መቀጠል፡፡ “አልችልም” የመጨረሻ ውሳኔ ሲሆን፣ “እስካሁን አልቻለኩም” ግንተስፋ ሰጪ ሃሳብ ነው፡፡
3. ካሉበት መጀመር
ብዙ ሰዎች ተስፋ የሚቆርጡት ሙሉውን ተራራ በአንድ ጊዜ ለመውጣት ስለሚሞክሩ ነው። “ይህን ሁሉ እንዴት በአንድ ጊዜ አደርጋለሁ?” ከማለት ይልቅ፣ “አሁን ማድረግ ያለብኝ ቀጣዩ እርምጃ ምንድነው?” ብሎ መጠየቅ ሂደቱን ያቀለዋል።
4. የማያውቅትን መማር
“አልችልም” ማለትን አቁመን ካለንበት ስንጀምር ሁኔታው እየጠራልን ይሄዳል፡፡ ማንበብ፣ መጠየቅ፣ ከሌሎች መማር፣ ልምድ ያለውን ሰው መከተል እና የመሳሰሉት ልምምዶች ያግዙናል፡፡
5. በውድቀት አለመገደብ
እርምጃ ካለ እንቅፋት አለ፡፡ እንቅፋት ካለ ደግሞ መውደቅ የማይቀር ነው፡፡ መውደቅ ካለ ደግሞ የግድ መነሳት መኖር አለበት፡፡ ስለዚህ አልችልም” ማለት ስህተት ነው። በዚያ ምትክ፣ “ይህ መንገድ አልሰራም፤ ስለዚህ ሌላ መንገድ መማር አለብኝ” ማለት ተመራጭ ነው።
6. ራስን ከሌሎች ጋር አለማነጻጸር
የሌሎችን ውጤት ከእኛ የጅማሬ ደረጃ ጋር ማነጻጸር ተስፋ ያስቆርጠናል፡፡ አንድ ሰው በአንድ መስክ ለ10 ዓመት ተለማምዶ የደረሰበትን ደረጃ አይተን መለስ ብለን ከእኛ ጅማሬ ጋር ማነጻጸር ትክክለኛ ሂደት አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር ካለመኖር ወደ መጀመር፣ ከመጀመር ደግሞ በብዙ ጥረት ወደ ማደግ ነው የሚሁደው፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

38
9September 2, 2026 2.8K 6 19