መሬት አስተዳደርን በማዘመን የክልሉን አርሶ አደሮች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብርና ቢሮ፣ በአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM P4R) ድጋፍ በብሔራዊ የገጠር መሬት መረጃ ስርዓት፣ በፕሮጀክት አስተዳደር፣ በክትትልና ግምገማ እንዲሁም መረጃ አስተዳደር ሥርዓት የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በግምገማው መድረክ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ፤ የመሬት አስተዳደር ተግባርን በማዘመን የክልሉን አርሶ አደሮች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በክልሉ 23 ወረዳዎች በአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM P4R) ድጋፍ የገጠር መሬት ምዝገባ መጀመሩን በመግለጽ፣ ከእነዚህም ውስጥ የ16 ወረዳዎች መረጃ ተጠቃሎ ወደ ብሔራዊ የገጠር መሬት መረጃ ስርዓት መመዝገቡን አስረድተዋል።
በዚህም 385 ሺህ ቁራሽ መሬት (ማሳ) ተለክቶ 220 ሺህ እማወራና አባወራዎች የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት መቻላቸውን አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል።
ከእነዚህ አርሶ አደሮች መካከል እስካሁን የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫን እንደ ዋስትና በማስያዝ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ ከፋይናንስ ተቋማት ብድር ማግኘት መቻላቸውንም ኃላፊው አስታውቀዋል።
የገጠር መሬት ምዝገባን በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ፣ በጥራት፣ በተጠያቂነትና ቅሬታዎችን በተገቢው መፍታት ልዩ ትኩረት የሚፈልግ መሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ዮሐንስ፤ መሬት ለአርሶ አደሩ የኢኮኖሚ መሠረት እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሀብት ነው ብለዋል።
መድረኩ በብሔራዊ የገጠር መሬት መረጃ ሥርዓት ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑን በቢሮው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ታደሰ ገልጸዋል።
ስለሆነም የሚከናወኑ ማንኛውም የመሬት ግብይት እንቅስቃሴዎች በአግባቡ፣ በተጠያቂነት፣ በሙያ ስነ-ምግባር እንዲሁም በቴክኖሎጂ ታግዘው በየቀኑ መተግበር እንዳለባቸውም አቶ አበበ ጠቁመዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
📌በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
📌በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
📌በትሬድስ
https://www.threads.com/@southwest_communications
📌በብሉ ስካይ
https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social
በደብልው ኤን ሶሻል
https://wnsocial.com/page/16775











