የኅብረ ብሔራዊነቷ ትልቅነትና የታሪክ ምዕራፍ፦ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ያስተላለፉት መልዕክት
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው ሀገራዊ ምክክር ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ የሚሆን ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል::
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኦባሳንጆ፣ ለዚህ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ መሳካት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል



















