ዘመነ በሰራቸው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች ምክንያት የአማራ ወጣቶች ለሕልውናቸው እየተዋጉ ሕዝባቸውን… — ራስ አማራ|Ras se'ela kirstos — TG.ME

ዘመነ በሰራቸው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች ምክንያት የአማራ ወጣቶች ለሕልውናቸው እየተዋጉ ሕዝባቸውን ከጥቃት የሚከላከሉበትን የፋኖ መከላከያ ሰራዊት መስርተዋል ። ዘመነ ካሴ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ሆኖ የአማራን ወጣት ከባድ መሳሪያ አስታጥቆታል ። በጎንደር ፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎጃም ያሉ ወጣቶች በዘመነ ካሴ፣ በአሳምነው ጽጌ፣ በምህረት ወዳጆ/ ምሬ/ ስም እየማሉ የሕዝባቸው የህልውና ጠባቂ ሆነዋል። መማርና መነገድ፤ እየቻሉ ወደ ህልውና ትግል የገቡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ወጣቶች አርአያ ያደረጉት እነ ዘመነ ካሴን ነው።

የዳንኤል ከንቱ የ 104 ገጾች ስድብም ስድብ ሆኖ ይቀራል። በወለጋና በመተከል በቡራዩና በአጣዬ፤ በሻሸመኔና አርሲ የተጨፈጨፈው አማራ ነፍጥ ለማንሳት ምክንያት እንደሌለው ተደርጎ የተቆጠረው በቤተ መንግስቱ ዳንኤልና በእሱ አለቆች ብቻ ነው። አማራ በሰልፍ የጠየቀውን መብት ሲያጣ ሰይፍ አነሳ ብሎ ለማስረዳት ህሊናን ማሰራት ይጠይቃል።

በራሪ ጀት እና ድሮን ያላስቆመውን ግዙፍ የሕዝብ ትግል በራሪ መጽሐፍ ይቀለብሰዋል ብሎ ማሰብ የተገባ አይደለም !!!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
ከቂሊንጦ ማ/ቤት
👍7❤2
August 25, 2024 3K 1