የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ: post #2491 — TG.ME

የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባPhoto
የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው መሆናቸው ተገለጸ።

አዲስ አበባ| ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ውጤቶች የለውጡ እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸው ተግባራት መሆናቸውን የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናገሩ። ምክትል ኮሚሽነሯ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ወቅት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም እና ያለፉት 5 ዓመታት የስራ አፈፃጸም ግምገማ ከሰኔ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኮሚሽኑን የስራ አፈፃጸም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ፤ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የህዝብ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ በርካታ ዘርፈ ብዙና ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት ስኬታማ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቀዳሚ መሪነት የተጀመረው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ እምርታ ማሳየቱን ምክትል ኮሚሽነሯ አብራርተዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ቀደም ሲል ከነበረበት የግለሰብ ቤቶች እድሳት ደረጃ በመውጣት፣ በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የሆኑ የ"በጎነት መንደር" ግንባታዎችን ወደ ማካሄድ መሸጋገሩንና በከፍተኛ ደረጃ መስፋቱን አስረድተዋል።

ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት ውስጥ ብቻ በዚህ በጎ እሳቤ ተመርቶ በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የዜጎችን ማኅበራዊ አኗኗር የሚመጥኑና የከተማዋን ገጽታ ያዘመኑ ከ46 ሺህ 441 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ወ/ሮ ፀሐይ ገልጸዋል። አያይዘውም ይሄው አበረታች የበጎ ፈቃድ ስራ በሚቀጥለው የ2019 በጀት ዓመትም ከከተማዋ ሁለንተናዊ እድገትና ለውጥ ጋር ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ፣ ይበልጥ በላቀ የሰው ተኮር እሳቤ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2 ሺህ 500 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኛ ወገኖች ለመገንባት ታቅዶ ርብርብ እየተደረገበት እንደሚገኝና ስራዎችም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተቋሙ "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሚመሩት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የነዋሪውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው።

#በጎነት_ለአዲስ_አበባ_ከፍታ
#የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት
#humanitarian
#አዲስ_አበባ
#Ethiopia
👍2
July 18, 2026 370 1